Categories
Amharic

የኮቪድ- 19 ወረርሽኝን ለመከላከል የህይወት ዋጋ በመክፈል ሲሰሩ ለነበሩ የጤና ባለሙያዎች እና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ሀገራዊ የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ተጀመረ

በዚህ የምስጋና እና የእውቅና ፕሮግራም ላይ በክብር እንግድነት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተገኝተዋል።

የጤና ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ሊያ ታደሰ በምስጋና ኘሮግራሙ ላይ ሀገር ጭንቅ ውስጥ በነበረችበት ጊዜ  ለህይወታቸውን ሳይሳሱ ፣ ምቹ ሁኔታ ባልነበረበት ለሰሩ የጤና ባለሙያዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኢትዩጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኮቪድ-19 ምላሽ ላደረገው የተለያየ ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ የምስጋና እና የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል።

በተለየ መልኩ ለኮቪድ-19 የመከላከል እና መቆጣጠር ስራዎችን ሲሰሩ ለነበሩት እንዲሁም እየሰሩ ለሚገኙት

የብሔራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ-19 ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል ሰራተኞች እና የጤና ባለሞያዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሳምንቱን በመሉ ለ24 ሰአት ሲያደርጉት ስለነበረው እና እያደረጉትም ስላሉት ተግባራት እውቅና ተሰጥቷል።

ለኢትዩጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ለብሔራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ-19 ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል የተበረከተውን የእውቅና እና ምስጋና ሽልማት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳሬክተር እና የኮቪድ-19 ምላሽ ዋና አስተባባሪ አቶ አስቻለዉ አባይነህ በክብር ተረክበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ለክልል መስተዳድሮች ፣ ለክልል ጤና ቢሮዎች ፣ ለጤና ተቋማቶች ፣ ለድርጅቶች ፣ ኤጀንሲዎች ፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ የተለያዩ ተቋማቶች

የምስጋና እና የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።

እንዲሁም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ የጤና ባለሞያዎች ለቤተሰቦቻቸው የማስታወሻ እና የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ለጤና ባለሞያዎች እና ለድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የሚሰጠው የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም በሀገር አቀፍ ደረጃ  እና በተለያዩ ድርጅቶች ለአንድ ሳምንት ይከበራል።

ኮቪድ-19 አሁንም ስጋት ሆኖ የቀጠለ በመሆኑ ወረርሽኙ እንደገና እንዳያንሰራራ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያሳስባል።

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *