Categories
Amharic

ታሪክን ስንዘክር ታሪክ የሚያስተላልፍ ትውልድን በመጠበቅ ይሁን!!!

የኮቪድ-19 በሽታ በማንኛውም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን በብዙ ህመም ውስጥ እንዲገኙ አልፎም ለብዙዎች ህይወት ህልፈት ምክንያት ሆኗል፡፡ ለትውልድ ታሪክ፣ ቅርስ እና ባህልን የሚያስተላልፉልን በተለይም እድሜያቸው ከ55 በላይ የሆኑ  አባቶቻችን እና እናቶቻችን በበሽታው ምክንያት ህይወታቸውን በየቀኑ ከሚያልፉት መካከል ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ የትላንት ታሪካችንን የሚያስተምሩልን፣ ለዛሬ ማንነታችን መሰረት የሆነውን ባህላችን  ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያሻግሩትን ታላላቆቻችን ጀግኖችን በምንዘክርበት በዚህ ወቅት ጤናቸውንም እንጠብቅ ዘንድ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡

ባሳለፍናቸው ሁለት ወራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሌሎች ሀገራት መቀነስን ቢያሳይም ይህ ግን በእኛ ሀገር የተቃራኒውን መንገድ ይዞ በመገስገስ ላይ ይገኛል፡፡ እንደማሳያነት በአህጉራችን ግንባር ቀደም የኮቪድ-19 ቁጥር ሪፖርት የምታደርገው ደቡብ አፍሪካ በተከተሉት ጥብቅ የመከላከያ መንገዶች በጥር ወር ውስጥ በቀን እስከ 21,000 በቫይረሱ የተያዙ እና 755 ግለሰቦች  ሞት በመቀነስ በየካቲት ወር 1,168 በቫይረሱ የተያዙግለሰቦች እና 157 ግለሰቦች ሞት  ሪፖርት ማድረግ ችለዋል፡፡ ይህም ከሚያዙት የሰው ቁጥር 15 እና ከሚሞቱት ሰዎች 5 እጥፍ ለውጥ ያሳያል፡፡

በሀገራችን  ወረርሽኙን ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ያለ ሲሆን እንደምሳኔነት  እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ ንቅናቄ እና የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፤ባሳለፍነው ወራት የተስተዋሉት በየጊዜው በመቀነስ ላይ የሚገኝው የኮቪድ-19 መከላከያ መንገድ ትግበራ፣ የሰው መሰባሰብ የሚበዛባቸው በዓላት፣ ሰርግን ጨምሮ ያሉ የማህበራዊ የኑሮ ዝይቤዎች፣ የመንገድ ላይ ሰልፎች እንዲሁም ሌሎችም የኮቪድ-19 ስርጭትን እንዲጨምር ምክንያት ከሆኑት ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ባሳለፍነው የፈረንጆች የጥር ወር ውስጥ ከተደረጉ 144,587 ምርመራዎች 12,028 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን 145 የህይወት ህልፈቶችም በዚህ ወር ተመዝግቧል፡፡ በየካቲት ወር ከተደረጉ 172,035 ምርመራዎች ውስጥ 21,422 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ እና 272 ህልፈቶች ሪፖርት ተደርጓል፡፡ እነዚህንም ወራት በምናወዳድርበት ወቅት የተያዙ ሰዎች ቁጥር 78 በመቶ እንዲሁም በሞት ቁጥር 88 በመቶ መጨመር አሳይቷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ቫይረስ  የሚያዙ  ሰዎች ቁጥር ፤ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እንዲሁም  በኮቪድ -19 ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ  በመምጣቱ እያንዳንዱ ግለሰብ፤ ቤተሰብ፤ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ የሐይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ የጤና ባለሙያዎች፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት  ማስክ ማድረግ ፣ የእጃቸውን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ  ተገቢውን ጥንቃቄ እዲያደርጉ  የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያሳስባል፡፡

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#COVID19Ethiopia

#NOMASKNOSERIVCE  

Categories
English

Status update on COVID19 Ethiopia February 28, 2021

Categories
Amharic

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ የካቲት 21,2013

Categories
English

Status update on COVID19 Ethiopia February 27, 2021

Categories
Amharic

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ የካቲት 20,2013

Categories
English

Status update on COVID19 Ethiopia February 26, 2021

Categories
Amharic

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ የካቲት 19,2013

Categories
Amharic

ትኩረት ለ ኮቪድ-19

በአለም ዙሪያ በየደቂቃው በኮቪድ-19 የሚያዙ እና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡

በኢትዮጵያ  እስካሁን 2‚128‚036 የኮቪድ -19 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 158‚053 ግለሰቦች ላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ፤ በትላንትናው ዕለት 14 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን እስካሁን 2‚354 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት ከተመረመሩት 6‚759 ውስጥ 1‚006 ግለሰቦች  ቫይረሱ ሲኖርባቸው፤ ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች 15 ግለሰቦች ወይም (15%)  መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህን ያህል  ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዙት በማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ (COMBAT) ወቅት ነው፡፡ ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ፤ የማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ (COMBAT) ከመጀመሩ በፊት እንዲሁም በኃላ በቀን የዚህን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ተመዝግቦ አያውቅም፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ቫይረስ  የሚያዙ  ሰዎች ቁጥር ፤ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እንዲሁም  በኮቪድ -19 ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ  በመምጣቱ እያንዳንዱ ግለሰብ፤ ቤተሰብ፤ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ የሐይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ የጤና ባለሙያዎች፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት  ማስክ ማድረግ ፣ የእጃቸውን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ  ተገቢውን ጥንቃቄ እዲያደርጉ  የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያሳስባል፡፡

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#COVID19Ethiopia #NOMASKNOSERIVCE  

Categories
Amharic

ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተሰጠ ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ያገኛል፡፡ከዚህም ውስጥ የላብራቶሪ ማስፋፊያ ስራ አንዱ ነው፡፡በተሰራው የላብራቶሪ ማስፋፊያ ስራ  ከአንድ ላብራቶሪ ምርመራ ተቋም በመነሳት በምርምር ተቋማት፤በክልል ላብራቶሪዎች ፤ በዩኒቪርቲዎች እንዲሁም ከግል ተቋማት ጋር በመተባበር የ ኮቪድ-19 ምርመራ ተቋማትን ማስፋፋቱ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረት የግል ተቋማት አስፈላጊውን መስፈርት ካሟሉ በኃላ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ፍቃድ ይሰጣቸዋል። ይህንን ፍቃድ ካገኙ 15 የግል ተቋማት 13 ነባር የግል ተቋማት ሲሆኑ 2 አዲስ መስፈርቱን አሟልተው  የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እና የውጤት የሰርተፊኬት የሚሰጡ የግል ተቋማት በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡

ይሁን እንጂ በቅርቡ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እናደርጋለን እስከ 6 ሰዓትም ውጤት እናሳውቃለን እያሉ ማስታወቂያ የሚያሰራጩ ተቋማት መኖራቸውን ደርሰንበታል፡፡

ስለሆነም ተገቢውን መስፈርት ሳያሟሉ ምርመራ እናደርጋለን የሚሉ ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማህበረሰቡም መስፈርቱን አሟልተው እውቅና በተሰጣቸው ተቋማት ብቻ አገልግሎት እንዲያገኙ እያሳሰበ አዲስ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋማት ሲኖሩ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ መስፈርቱን አሟልተው የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ የሚሰጡ የግል ተቋማት ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ናቸው።

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#COVID19Ethiopia

#NOMASKNOSERIVCE  

Categories
Amharic

ዳግም ትኩረት ለኮቪድ-19

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ  ተይዘው  ህይወታቸውን የሚያጡ  ግለሰቦች  ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፡በትላንትናው እለት ብቻ 19 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፤ 15ቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡በኢትዮጵያ ከመስከረም 12 ወዲህ በትላንትናው እለት የተመዘገበው የሞት  ቁጥር ከፍተኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ እስካሁን 2‚340 ግለሰቦች በኮቪድ -19 ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ከእነዚህም ውስጥ 1‚716 ወይም (73%) ከአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡

በትላንትናው እለት 6‚659  ግለሰቦች ናሙና የሰጡ ሲሆን  ከዚህም  ውስጥ 935 ግለሰቦች   የኮቪድ -19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች  14 ግለሰቦች ወይም (14%) በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡  የኮቪድ -19 የስርጭት ምጣኔ በኢትዮጵያ ከጥር 28 እስከ ትላንትናው እለት ድረስ  ከ10% በላይ ሆኖ  ተመዝግቧል፤ በዚህም መሰረት ከ አፍሪካ  በኮቪድ -19 ከ10% በላይ የስርጭት ምጣኔ ከሚይስመዘግቡ ጥቂት ሀገራት ተርታ ኢትዮጵያን ያስመድባታል፡፡

በመሆኑም እያንዳንዱ ግለሰብ፤ ቤተሰብ፤ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ የሐይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ የጤና ባለሙያዎች፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተደጋግሞ የሚገለጹትን የመከላከያ መንገዶችን ማለትም  ማስክ ማድረግ፣ አዘውትሮ እጅን በሳሙና ና በውሃ በአግባቡ መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር በማፅዳት  እና አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ራሳቸውን ፣ ቤተሰቦቻቸውን እና ማህበረሰቡን ከበሽታው እንዲከላከሉ እና ሀላፊነታቸውን የኢትጵዮያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#COVID19Ethiopia

#NO MASK NO SERIVCE