Categories
Amharic

ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተሰጠ ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ያገኛል፡፡ከዚህም ውስጥ የላብራቶሪ ማስፋፊያ ስራ አንዱ ነው፡፡በተሰራው የላብራቶሪ ማስፋፊያ ስራ  ከአንድ ላብራቶሪ ምርመራ ተቋም በመነሳት በምርምር ተቋማት፤በክልል ላብራቶሪዎች ፤ በዩኒቪርቲዎች እንዲሁም ከግል ተቋማት ጋር በመተባበር የ ኮቪድ-19 ምርመራ ተቋማትን ማስፋፋቱ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረት የግል ተቋማት አስፈላጊውን መስፈርት ካሟሉ በኃላ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ፍቃድ ይሰጣቸዋል። ይህንን ፍቃድ ካገኙ 15 የግል ተቋማት 13 ነባር የግል ተቋማት ሲሆኑ 2 አዲስ መስፈርቱን አሟልተው  የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እና የውጤት የሰርተፊኬት የሚሰጡ የግል ተቋማት በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡

ይሁን እንጂ በቅርቡ የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ እናደርጋለን እስከ 6 ሰዓትም ውጤት እናሳውቃለን እያሉ ማስታወቂያ የሚያሰራጩ ተቋማት መኖራቸውን ደርሰንበታል፡፡

ስለሆነም ተገቢውን መስፈርት ሳያሟሉ ምርመራ እናደርጋለን የሚሉ ተቋማት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማህበረሰቡም መስፈርቱን አሟልተው እውቅና በተሰጣቸው ተቋማት ብቻ አገልግሎት እንዲያገኙ እያሳሰበ አዲስ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋማት ሲኖሩ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ መስፈርቱን አሟልተው የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ የሚሰጡ የግል ተቋማት ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ናቸው።

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#COVID19Ethiopia

#NOMASKNOSERIVCE  

Categories
Amharic

ዳግም ትኩረት ለኮቪድ-19

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ  ተይዘው  ህይወታቸውን የሚያጡ  ግለሰቦች  ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፡በትላንትናው እለት ብቻ 19 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፤ 15ቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡በኢትዮጵያ ከመስከረም 12 ወዲህ በትላንትናው እለት የተመዘገበው የሞት  ቁጥር ከፍተኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ እስካሁን 2‚340 ግለሰቦች በኮቪድ -19 ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ከእነዚህም ውስጥ 1‚716 ወይም (73%) ከአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡

በትላንትናው እለት 6‚659  ግለሰቦች ናሙና የሰጡ ሲሆን  ከዚህም  ውስጥ 935 ግለሰቦች   የኮቪድ -19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች  14 ግለሰቦች ወይም (14%) በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡  የኮቪድ -19 የስርጭት ምጣኔ በኢትዮጵያ ከጥር 28 እስከ ትላንትናው እለት ድረስ  ከ10% በላይ ሆኖ  ተመዝግቧል፤ በዚህም መሰረት ከ አፍሪካ  በኮቪድ -19 ከ10% በላይ የስርጭት ምጣኔ ከሚይስመዘግቡ ጥቂት ሀገራት ተርታ ኢትዮጵያን ያስመድባታል፡፡

በመሆኑም እያንዳንዱ ግለሰብ፤ ቤተሰብ፤ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ የሐይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ የጤና ባለሙያዎች፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተደጋግሞ የሚገለጹትን የመከላከያ መንገዶችን ማለትም  ማስክ ማድረግ፣ አዘውትሮ እጅን በሳሙና ና በውሃ በአግባቡ መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር በማፅዳት  እና አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ራሳቸውን ፣ ቤተሰቦቻቸውን እና ማህበረሰቡን ከበሽታው እንዲከላከሉ እና ሀላፊነታቸውን የኢትጵዮያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#COVID19Ethiopia

#NO MASK NO SERIVCE  

Categories
Amharic

በሞባይል መተግበሪያ የሚሰጠው የኮቪድ-19 ስልጠና በአዲስ መልክ ቀረበ

ኮቪደ-19 ኢትዮጵያ በሚባል የሚታወቀው የስልጠና መተግበሪያ በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን ከምንጠቀምበት የኮቪድ-19 መመሪያዎች ባማከለ መልኩ በተጨማሪ የትምህርት ቤት እና የቤት ውስጥ እንክብካቤ ጨምሮ በአዲስ መልክ ቀርቧል፡፡ስልጠናውን ይውሰዱ፣ ሰርተፍኬት ያግኙ!
http://bit.ly/3apv5J2
COVID-19 Ethiopia has been updated COVID-19 Ethiopia, a platform to train health workers have been updated according to the current guideline with additional courses on COVID-19 prevention at school setting and for home-based isolation and care.
Train and earn your certificate!
http://bit.ly/3apv5J2 Supporting Video can be found by clicking here.

Categories
Amharic

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ አስከፊነቱ እየጨመረ ይገኛል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ አስከፊነቱ እየጨመረ ይገኛል፡፡ ባለፉት 7 ቀናት (ከየካቲት11 – የካቲት17) 47,204 ናሙና ከሰጡት ግለሰቦች ውስጥ 5,927 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፡፡ በእነዚህም 7ቀናት (ከየካቲት11 – የካቲት17) ከተመረመሩት ከመቶ 13 ግለሰቦች (13%) የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል ማለት ነው።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተይዘው ወደ ፅኑ ህሙማን ህክምና ክፍል የሚገቡ ግለሰቦች  ቁጥርም ከእለት ወደ እለት እያሻቀበ ይገኛል። እስከ ትላንትናው እለት ብቻ 386 ሰው በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 61 ህሙማን  በ መተንፈሻ ማሽን ላይ ይገኛሉ፡፡ በቫይረሱም ህይወታቸውን የሚያጡ  ግለሰቦች  ቁጥርም እየጨመረ ሲሆን እስካሁን 2,316  ግለሰቦች በኮቪድ -19 ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ በዚህ 7 ቀናት ብቻ የ79 ግለሰቦች ህይወት አልፏል፡፡

ሕብረተሰቡ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ይህንን እውነታ በመገንዘብ አሁንም የጥንቃቄ መንገዶችን በሚገባ መተግበር እንዳለባቸው የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያስገነዝባል።

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#COVID19Ethiopia #NOMASKNOSERIVCE 

Categories
Amharic

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው!!

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ   በፍጥነት በአለም አቀፍ ደረጃ ብሎም በሀገራችን እየተዛመተ ይገኛል፡፡ በእኛ ሀገር የስርጭት ሁኔታ ስንመለከት በትላንትናው እለት ብቻ ናሙና ከሰጡ 6,089 ግለሰቦች መካከል 977 ያህሉ በኮቪድ-19 ተይዘዋል፡፡

ይህም ማለት ናሙና ከሰጡት 100 ግለሰቦች 16ቱ(16%) በቫይረሱ  እንደተያዙ ያሳያል፡፡ይህ ቁጥር በባለፈው  ሳምንት ( የካቲት 14) ለመጀመሪያ ጊዜ የተመዘገበ ሲሆን በትላንትናው እለትም ለሁለተኛ ጊዜ ተመዝበግዋል:: ይህ የሚያሳየው የኮቪድ-19 ስርጭት በሀገራችን ምን ያህል አስጊ እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ነው፡፡ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣው በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ክልሎች ጭምር ነው፡፡ለማሳያነት በትላንትናው እለት የሶስት  ክልሎችን ብናይ በአዲስ አበባ ናሙና ከሰጡ 4614 ግለሰቦች መካከል 854 ግለሰቦች ወይም 19 በመቶ (19%) የተያዘ ሲሆን ፤ በኦሮሚያ ክልል ናሙና ከሰጡ 286 ግለሰቦች 70 የሚሆኑት ወይም 24 በመቶ (24%) መያዛቸውን ያሳያል፤እንዲሁም በሲዳማ ክልል ናሙና ከሰጡ 85 ግለሰቦች 21 ግለሰቦች ወይም 25 በመቶ  (25%) ቫይረሱ እንዳለባቸው ያሳያል፡፡ ይህ አሀዝ የሚያሳየው የ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በክልሎችም በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መምጣቱን ነው፡፡

ወደ  ፅኑ  ህሙማን ህክምና ክፍል የሚገቡ ግለሰቦች  ቁጥርም እየጨመረ ይገኛል፡፡እስከ ትላንትናው እለት ብቻ 386 ግለሰቦች ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የገቡ ሲሆን፤ ወደ ህክምና ማዕከል ከሚገቡት 100 ግለሰቦች 70 ግለሰቦች(70%) የሚሆኑት በተለያየ መጠን ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ በትላንትናው ዕለት ብቻ  ፅኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው 61 ቫይረሱ የተገኝባቸው ግለሰቦች ተመዝግብዋል፤ ይህ ቁጥር ከነሐሴ 2012  በሁላ የመጀመሪያ ከፍተኛ ቁጥር ነው፡፡

የሞት ምጣኔውንም ስናይ ደግሞ እስከ ትላንትናው እለት ብቻ 2,316 ግለሰቦች ህይወት አልፏል ይህ ማለት በዚህ ሳምንት ብቻ በአማካኝ በቀን 11 ግለሰቦች ህይወታቸውን በኮቪድ -19 እያጡ ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም እያንዳንዱ ግለሰብ፤ ቤተሰብ፤ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ የሐይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ የጤና ባለሙያዎች፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከከልና ለመቆጣጠር ተግባር ላይ በባለቤትነት እና በኃላፊነት ስሜት አጠናክረው እንዲሠሩ እናሳስባለን፡፡ 

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#COVID19Ethiopia

#NOMASKNOSERIVCE  

Categories
English

Status update on COVID19 Ethiopia February 25, 2021

Categories
Amharic

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ የካቲት 18,2013

Categories
Amharic

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ የካቲት 17,2013

Categories
English

Status update on COVID19 Ethiopia February 24, 2021

Categories
English

Status update on COVID19 Ethiopia February 23, 2021