Categories
Amharic

በኢትዮጵያ ሦስተኛው ዙር የኮቪድ-19 (3rd Wave) ወረርሽኝ እየጀመረ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ ነው

የኮቪድ-19 ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰቱ ከታወቀ ጊዜ ጀምሮ እስከ (ሐምሌ 22/2013) ለ3,006,482 ግለሰቦች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 279,629 ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 263,392 ግለሰቦች ከኮቪድ-19 ቫይረስ አገግመዋል። 4,381 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በተለያዩ የዓለም ሀገራት መረጃዎች እና ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሦስተኛው ዙር (3rd Wave) የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰቱ ታውቋል። ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው የኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ነው። በሀገራችን የኮቪድ-19 የዴልታ ቫይረስ መኖሩ ባይረጋገጥም የሶስተኛ ዙር (3rd Wave) ወረርሽኝ መከሰቱን የሚያሳዩ ምልክቶች መታየት ጀምሯል።

እንደ ማሳያነት ከዛሬ ሶስት ሳምንት በፊት በኮቪድ-19 ቫይረስ የሚያዙ ግለሰቦች ቁጥር ዝቅተኛ ነበረ። በአማካኝ በአንድ ቀን 70 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ ተይዘው ሪፖርት ይደረግ የነበረ ሲሆን ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መጥቶ (ሐምሌ 22/2013) 476 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ይህም ቁጥር ሁለተኛው ዙር (2nd wave) ካበቃበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግበዋል፡፡ ናሙና ከሚሰጡ 100 ግለሰቦች 1 እስከ 2 ግለሰቦች የመያዝ ምጣኔ የነበረ ሲሆን (ሐምሌ 22/2013) ከሶስት እጥፍ በላይ ጨምሮ ወደ 7 ግለሰቦች የመያዝ ምጣኔ ከፍ ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ የሚገኙ ህሙማን ከሶስት ሳምንት በፊት በአማካኝ 124 ግለሰቦች የነበሩ ሲሆን (ሐምሌ 22/2013) በእጥፍ በመጨመር ወደ 228 ከፍ ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የጤና ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት  ጋር በመተባበር እንዲሁም ማህበረሰቡን በማሳተፍ የኮቪድ-19 ቫይረስ በሀገራችን ከመከሰቱ በፊት የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን በመስራትና በማስተባበር ከተከሰተም በኋላ የተለያዩ የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም ሁለተኛው ዙር (2nd wave) ካበቃ በኋላ በተወሰነ መልኩ በማህበረሰቡ የታዩ መዘናጋቶች እንዲሁም የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በአግባቡ ባለመተግበራቸው ሶስተኛ ዙር (3rd wave) ሊከሰት የሚችልበት ምልክቶች እየታዩ ስለሆነ እያንዳንዱ ግለሰብ ፣ ቤተሰብ ፣ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ የሐይማኖት ተቋማት ፣ ሲቪክ ማህበራት ፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣ የጤና ባለሙያዎች ፣ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ማስክ ማድረግ፣የእጅን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ እና ርቀትን በመጠበቅ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የኮቪድ-19 መከላከከልና መቆጣጠር ተግባር ላይ በባለቤትነት እና በኃላፊነት ስሜት አጠናክረው እንዲሠሩ እናሳስባለን፡፡ 

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

Categories
Amharic

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ሐምሌ 22 2013

Categories
English

Status update on COVID19 Ethiopia July 29, 2021

Categories
Amharic

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ሐምሌ 21 2013

Categories
English

Status update on COVID19 Ethiopia July 28, 2021

Categories
English

Status update on COVID19 Ethiopia July 27, 2021

Categories
Amharic

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ሐምሌ 20 2013

Categories
English

Status update on COVID19 Ethiopia July 26, 2021

Categories
English

Status update on COVID19 Ethiopia July 25, 2021

Categories
Amharic

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ሐምሌ 18 2013