Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ግንቦት-20

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4950 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ (100) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ስምንት መቶ ሰላሳ አንድ (831) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 53 ወንድ እና 47 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ 3 እስከ 70 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ዘጠና ዘጠኝ ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንድ ሰው የብሩንዲ ዜጋ ነው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ዘጠና አራት (94) ሰዎች ከአዲስ አበባ (ሰላሳ አራት በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው እና ስልሳ ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው) ፣ አንድ (1) ሰው ከትግራይ ክልል (የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው እና በለይቶ ማቆያ ያለ) ፣ ሁለት (2) ሰዎች ከሶማሊ ክልል (የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው እና በለይቶ ማቆያ ያሉ) እንዲሁም ሶስት (3) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል (አንድ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያለው እና ሁለት የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው) ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተጋላጭነት ሁኔታቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው3
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው35
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው የታወቅጋር ግንኙነት የሌላቸው62
 ድምር100

በተጓዳኝ ህመም ምክንያት ህክምና ላይ የነበሩ የ70 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት ለኮሮና ቫይረስ በሽታ በተደረገ ምርመራ ናሙና ከተወሰደ በኋላ የምርመራ ውጤት ሳይደርስ ህይወታቸው አልፏል። በምርምራው ውጤትም ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ስለተረጋገጠ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባት (7) ደርሷል፡፡ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡  

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስር (10) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ዘጠና አንድ (191) ነው።

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ96,566
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ4950
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ100
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ631
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ1
አዲስ ያገገሙ10
በአጠቃላይ ያገገሙ191
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ7
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር831

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።   

  • መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
  • መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 20 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *