ኮቪድ-19 በአለማችን ከተከሰተ ዕለት አንስቶ እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለከፋ ህመም ፣ ለበርካቶች ደግሞ ህልፈተ ህይወት ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን አስከትሏል፡፡ በሃገራችን አንድ በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዘ ግለሰብ ከተመዘገበበት ዕለት መጋቢት 4/2012 ጀምሮ 230‚944 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፣171,980 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፤983 ሰዎች በፅኑ ህሙማን ክፍል ይገኛሉ። እንዲሁም 3‚208 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ባሳለፍነው 7 ቀናት (መጋቢት28- ሚያዝያ 04/2013) 183 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡በዚሁ ሳምንት አዲስ አበባን ጨምሮ ከፍተኛ የሞት ቁጥር ያስመዘገቡ ክልሎችን ስንመለከት:-
*አዲስ አበባ 98
*ኦሮሚያ 30
*አማራ 14
*ሐረሪ 14
*ሲዳማ 10 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ሁሉም የማሕበረሰብ ክፍል የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም ፣ የእጅን ንጽህና በተደጋጋሚ በመጠበቅ እና በማንኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ አዘውትረን የኮቪድ-19 የመከላከያ መንገዶችን እንድንተገብር የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያሳስባል፡፡
#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ
#COVID19Ethiopia
#Directive30
#COVID19VACCINE
#NOMASKNOSERIVCE