Categories
Amharic

የ2014 ዓ.ም አዲሱን ዓመት አስመልክቶ በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

እንኳን ለ2014 ዓ.ም አደረሳችሁ እያልን በዓለም አቀፍ ደረጃና በሃገራችን የኮቪድ-19 ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱ እና ቫይረሱ ባህሪውን እየቀያየረ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ህይወታቸውን አጥተዋል ፡፡

የ2014 አዲስ ዓመት መቀበያ በዓልን አተከትሎ በሚኖር የቤተሰብ ጥየቃ ምክንያት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፣ በግብይት ቦታዎች፣ በሉኳንዳ ቤቶች፣ በመዝናኛ ስፍራዎች የሚደረጉ መሰባሰቦች አዲሱን የኮቪድ-19 ‘ዴልታ’ ዝርያ መኖር ጋር ተዳምሮ የቫይረሱ መሰራጨት ምክንያት ስለሚሆኑ፡-

* በማንኛውም ምክንያት የሚፈጠሩ መሰባሰቦችን በማስቀረትና ባለመገኘት፣

* በዘመድ/ቤተሰብ ጥየቃ ከቦታ ቦታ የሚደረግን እንቅስቃሴን በማስቀረት፣

 *በማንኛውም ጊዜና ቦታ ማስክ ማድረግ፣

 *እጅን በሳሙናና በውሃ አዘውትሮ መታጠብ እና በሳኒታይዘር በማፅዳት፣

 *አካላዊ ርቀታችን መጠበቅ፣

 *የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የቫይረሱን ስርጭት እንከላከል!

አዲሱ ዓመት የኮቪድ-19 ቫይረስ ወረርሽኝ ከዓለማችንና ከሃገራችን ተወግዶ የምናይበት፣ ሀገራችን ከሰው ሰራሽ አደጋዎች ተጠብቃ ያሰብነውን የምናሳካበት እንዲሁም ዓመቱ የሰላም፣ የደስታ፣ የመተሳሰብና የፍቅር ዓመት እንዲሆን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለመላው የሃገራችን ህዝቦች ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል፡፡

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#መልካምአዲስአመት

#NEWYEAR

#COVID19Ethiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *