Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ግንቦት-1

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2383 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ ስድስት (16) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ አስር (210) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ 7 ወንድ እና 9 ሴት እንዲሁም እድሜያቸው ከ20 – 60 ዓመት የሆኑ ናቸው። የመኖሪያ ቦታቸው አዲስ አበባ የሆኑት 13 ሲሆኑ፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል (ወልድያ ለይቶ ማቆያ) እና 2 ከደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል (ወላይታ ሶዶ ለይቶ ማቆያ እና ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ) ይገኛሉ።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተጋላጭነት ሁኔታየታማሚዎች ቁጥር
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው2
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው13
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው1
 ድምር16

የላብራቶሪ ምርመራው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በአርማውር ሃንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በብሄራዊ የእንስሳት ጤና በሽታዎች ምርመራ ማዕከል፣ በኢትዮጲያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በነቀምት የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በአማራ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት (ባህር ዳር እና ደሴ) ፣ በደቡብ ብ/ብ/ሕ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላብራቶሪ፣ በአርሲ ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ፣ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ፣ በጅማ ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ሴንተር እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ  የተከናወነ ነው፡፡

በዛሬው ዕለት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ የ65 ዓመት የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ወንድ ኢትዮጵያዊ ህይወታቸው አልፏል ይህም በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አምስት (5) ደርሷል፡፡ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን  ሀዘን እየገለፁ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛሉ፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሁለት (2) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና ሰባት (97) ነው።

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ32,689
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ2383
በዛሬው  ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ16
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ106
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ0
አዲስ ያገገሙ2
በአጠቃላይ ያገገሙ97
በዛሬው ዕለት በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ1
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ5
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር210

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ ከሰዎች ጋር ሊኖረን የሚችሉ ግንኙነቶችን በመገደብ እና ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ መገኘታችን አስገዳጅ በሚሆንበት ሁኔታ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግ ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።  

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 1፣ 2012 ዓ.ም

Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ሚያዝያ-30

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1861 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መቶ ዘጠና አራት(194) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ሲሆኑ  እድሜያቸው ከ23-33 ዓመት የሆኑ ይገኙበታል። የሁሉም ታማሚዎች የመኖሪያ ቦታ አዲስ አበባ ነው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተጋላጭነት ሁኔታየታማሚዎች ቁጥር
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው0
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው2
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት በመጣራት ላይ ያለ1
 ድምር

የላብራቶሪ ምርመራው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በአርማውር ሃንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጲያ ባዮተክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በነቀምት የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በአማረ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላብራቶሪ፣ በአርሲ ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ፣ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ  የተከናወነ ነው፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሁለት (2) ሰዎች (1 ከአዲስ አበባ እና 1 ከኦሮሚያ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና አምስት (95) ነው።

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ30,306
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ1,861
በዛሬው  ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ3
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ93
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ1
አዲስ ያገገሙ2
በአጠቃላይ ያገገሙ95
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ4
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር194

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን  የዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ ከሰዎች ጋር ሊኖረን የሚችሉ ግንኙነቶችን በመገደብ እና ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ መገኘታችን አስገዳጅ በሚሆንበት ሁኔታ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግ ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።  

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ሚያዝያ 30፣ 2012 ዓ.ም

Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ሚያዝያ-28

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1382 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ ሰባት (17) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መቶ ስልሳ ሁለት (162) ደርሷል፡፡ የላብራቶሪ ምርመራው የተደረገው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በአርማውር ሃንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ ኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በአማራ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት (ባህር ዳር እና ደሴ)፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላብራቶሪ፣ በአርሲ ዩኒቨርስቲ ላቦራቶሪ፣ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ እና በጅማ ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ማዕከል የተከናወነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሁለት (2) ሰዎች  ከአዲስ አበባ  ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና ሶስት (93) ነው። የዕለቱ ታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታም እንደሚከተለው ቀርቧል፣

ተ.ቁዜግነትመኖሪያ ቦታእድሜፆታየውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክበበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት
1ኢትዮጵያዊአዲስ አበባ27ወንድየለውምየስራው ባህሪ ተጋላጭነት ያለው
2ኢትዮጵያዊ 20ወንድከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
3ኢትዮጵያዊ 25ወንድከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
4ኢትዮጵያዊ 14ወንድከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
5ኢትዮጵያዊ 26ወንድከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
6ኢትዮጵያዊ 65ወንድከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
7ኢትዮጵያዊአዲስ አበባ28ሴትየላትምያላት
8ኢትዮጵያዊአፋር (የተገኝው አዲስ አበባ)39ወንድየለውምበመጣራት ላይ ያለ
9ኢትዮጵያዊ 50ወንድከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
10ኢትዮጵያዊ 30ወንድከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
11ኢትዮጵያዊአዲስ አበባ53ሴትየላቻውምያላቸው
12ኢትዮጵያዊ 23ወንድከሶማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
13ኢትዮጵያዊ 24ወንድከሶማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
14ኢትዮጵያዊ 27ወንድከሶማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
15ኢትዮጵያዊ 20ወንድከሶማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
16ኢትዮጵያዊ 22ወንድከሶማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
17ኢትዮጵያዊ 41ወንድከሶማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ  የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ26,517
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ1,382
በዛሬው  ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ17
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ63
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ0
አዲስ ያገገሙ2
በአጠቃላይ ያገገሙ93
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ4
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር162

የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ ከመተግበር መዘናጋት እንደሌለበት ጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጥብቅ ያሳስባሉ፡፡ ሕብረተሰቡ በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግና አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል እናሳስባለን፡፡

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ሚያዝያ 28፣ 2012 ዓ.ም

Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ሚያዝያ-27

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1047 የላብራቶሪ ምርመራ አምስት (5) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መቶ አርባ አምስት (145) ደርሷል፡፡ የላብራቶሪ ምርመራው የተደረገው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላብራቶሪ፣ በአርሲ ዩኒቨርስቲ ላቦራቶሪ፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ እና በጅማ ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ማዕከል የተከናወነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ ስድስት (16) ሰዎች (15 ከአዲስ አበባ እና 1 ከአማራ ክልል)  ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና አንድ (91) ነው። የዕለቱ ታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታም እንደሚከተለው ቀርቧል፣

ተ.ቁዜግነትመኖሪያ ቦታእድሜፆታየውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክበበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት
1ኢትዮጵያዊአዲስ አበባ75ሴትየላቸውምበመጣራት ላይ ያለ (በጤና ተቋም  ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን ከተወሰደ ናሙና የተገኘ)
2ኢትዮጵያዊአፋር25ወንድከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
3ኢትዮጵያዊአፋር22ወንድከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
4ኢትዮጵያዊአዲስ አበባ8ሴትየላትምያላት
5ኢትዮጵያዊኦሮሚያ፣ ባቱ19ሴትየላትምያላት

ከላይ የተጠቀሱት የ75 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት በተጓዳኝ ህመም በሆስፒታል ውስጥ ተኝተው ሲታከሙ የነበሩ ሲሆን በገጠማቸው የመትንፈስ ችግር ምክንያት በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተጠርጥረው ምርመራ ናሙና ከተወሰደ በኋላ በምርመራ ውጤት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከመረጋገጡ በፊት ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል። የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ  የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ25,135
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ1047
በዛሬው  ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ5
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ48
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ0
አዲስ ያገገሙ16
በአጠቃላይ ያገገሙ91
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ4
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር145

የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ ከመተግበር መዘናጋት እንደሌለበት ጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጥብቅ ያሳስባሉ፡፡ ሕብረተሰቡ በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግና አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል እናሳስባለን፡፡

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ሚያዝያ 27፣ 2012 ዓ.ም

Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ሚያዝያ-26

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1758 የላብራቶሪ ምርመራ አምስት (5) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ  ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መቶ አርባ (140) ደርሷል፡፡ የላብራቶሪ ምርመራው የተደረገው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በብሄራዊ የእንስሳት ጤና በሽታዎች ምርመራ ማዕከል፣ በአርማውር ሃንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ላቦራቶሪ እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ የተከናወነ ነው፡፡ የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታም እንደሚከተለው ቀርቧል፣

ተ.ቁዜግነትመኖሪያ ቦታእድሜፆታየውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክበበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት
1ኢትዮጲያዊ24ወንድከፑንትላንድ የተመለሰና በጂግጂጋ  አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ 
2ኢትዮጲያዊ23ወንድከፑንትላንድ የተመለሰና በጂግጂጋ  አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ 
3ኢትዮጲያዊ20ወንድከፑንትላንድ የተመለሰና በጂግጂጋ  አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ 
4ኢትዮጲያዊባህር ዳር17ወንድ ያለው
5ስዊድናዊ (ትውልደ ኢትዮጵያዊ )19ወንድከስዊድን የተመለሰና በአዲስ አበባ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ 

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ  የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ24,088
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ1758
በዛሬው  ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ5
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ60
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ0
አዲስ ያገገሙ0
በአጠቃላይ ያገገሙ75
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ3
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር140

የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን  አዘውትሮ ከመተግበር መዘናጋት እንደሌለበት ጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጥብቅ ያሳስባሉ፡፡ ሕብረተሰቡ በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግና አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል እናሳስባለን፡፡

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት  በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ሚያዝያ 26፣ 2012 ዓ.ም

Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ሚያዝያ-25

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1560 የላብራቶሪ ምርመራ  ሁለት (2) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ  ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መቶ ሰላሳ አምስት (135) ደርሷል፡፡ የላብራቶሪ ምርመራው የተደረገው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በብሄራዊ የእንስሳት ጤና በሽታዎች ምርመራ ማዕከል፣ በኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በደቡብ ብ/ብ/ህ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ላቦራቶሪ እና በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሜዲካል ማዕከል ላብራቶሪ የተከናወነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ስድስት (6) ሰዎች ከድሬዳዋ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ሰባ አምስት (75) ነው፡፡ የዛሬው ዕለት የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታም እንደሚከተለው ቀርቧል፣

ተ.ቁዜግነትመኖሪያ ቦታእድሜፆታየውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክበበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት
1ኢትዮጲያዊባቱ/ዝዋይ (አዲስ አበባ ህክምና በመከታተል ላይ ያለ)49ወንድየለውምየለውም (በጤና ተቋም  ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን ከተወሰደ ናሙና የተገኘ)
2ኢትዮጲያዊስልጢ ወረዳ፣ስልጤ ዞን፣ ደቡብ ክልል45ሴትየላትምየላትም (በቤት ለቤት ቅኝትና አሰሳ የተለየች)

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ  የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ22,330
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ1560
በዛሬው  ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ2
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ55
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ0
አዲስ ያገገሙ6
በአጠቃላይ ያገገሙ75
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ3
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር135

የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን  አዘውትሮ ከመተግበር መዘናጋት እንደሌለበት ጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጥብቅ ያሳስባሉ፡፡ ሕብረተሰቡ በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግና አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል እናሳስባለን፡፡

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት  በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ሚያዝያ 25፣ 2012 ዓ.ም