Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ሰኔ-2

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4599 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ዘጠና (190) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2336 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 135 ወንድ እና 55 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 1 እስከ 89 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ ሃምሳ ሶስት (153) ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣አስራ ስድስት (16) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ አስር (10) ሰዎች ከአማራ ክልል፣ ሶስት (3) ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ ሶስት (3) ሰዎች ከሶማሊ ክልል፣ ሶስት (3) ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል እንዲሁም ሁለት (2) ሰዎች ከትግራይ ክልል ናቸው።

ማስተካከያ፦ በትላንትናው ዕለት ሪፖርት በተደረገው የዕለታዊ መግለጫ ቫይረሱ በምርመራ እንድተገኘባቸው ከተገለፁት ሰዎች መካከል አስር (10) ሰዎች ከዚህ ቀደም ሪፖርት ተደርገው በህክምና ማዕከል ውስጥ ያሉ እና ለክትትል ምርመራ የተደረገላቸው መሆናቸውን ከይቅርታ ጋር እንገልፃለን። በመሆኑም በትላንትናው ዕለት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ ስድስት (126) ናቸው።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአምስት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰላሳ-ሁለት (32) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡  ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከለው ቀርቧል፡፡

ተ.ቁየመኖሪያ አድራሻጾታዕድሜማብራሪያ
1አዲስ አበባወንድ42በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ
2አዲስ አበባወንድ40በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ
3አዲስ አበባሴት32በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ
4አዲስ አበባወንድ40በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ
5አዲስ አበባሴት85በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበሩ

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ ስምንት (18) ሰዎች (11 ከአዲስ አበባ፣5 ከአማራ ክልል እና 2 ከሶማሊ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 379 ነው።

የኮሮና ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ በቁጥር ከሚገለጸው በላይ ነው፡፡ ከእያንዳንዱ በየእለቱ ከምንገልጻቸው በቫይረሱ ከተያዙ ቁጥሮች ጀርባ የብዙ ቤተሰቦች እና ጓደኞቻቸው ጭንቀት እና ስጋት አለ፡፡

እርስዎም በዚህ ወቅት ቤተሰብ ባለመጠየቅዎ፣ ለቅሶ ባለመድረስዎ፣ ሰርግ ባለመታደምዎ፣ የወለዱ ጓደኞችዎን ወይም ዘመድዎን ባለመጠየቅዎ ወይም ከሚዎዷቸው ጋር ረፍትዎን አብረው ባለማሳለፍዎ ተጨንቀው እና አዝነው ይሆናል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ስለ ራስዎ፣ ስለሚዎዳቸው ብለውና ሕይወት ከኮቪድ-19 በኋላ በነጻነት እንደሚቀጥል በመረዳትዎ ስለሆነ አስተዋይ በመሆንዎ ሊበራታቱ ይገባዎታል፤ ሁሉም የሚጠበቅበትን በኃላፊነት በመወጣት ሊከሰት የሚችለውን የሕመም እና ሞት እንከላከል፡፡

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ152,334
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ4,599
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ190
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው1,923
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር32
አዲስ ያገገሙ18
በአጠቃላይ ያገገሙ379
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ32
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር2,336

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ሰኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *