Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ግንቦት-17

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2844 የላብራቶሪ ምርመራ ሰባ ሶስት (73) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ስድስት መቶ ሃምሳ አምስት (655) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 49 ወንድ እና 24 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ 6 እስከ 75 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 67 ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ቀሪዎቹ የተለያዩ ስድስት ሃገራት ዜጎች ናቸው።  ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሃምሳ ስድስት (56) ሰዎች ከአዲስ አበባ (አስራ ሶስት ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው፣ አስራ ሁለት ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው እና ሰላሳ አንድ ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው) ፣ አራት (4) ሰዎች ከትግራይ ክልል (ሁሉም የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው) ፣ ሁለት (2) ሰዎች ከአማራ ክልል (በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው) ፣ ስምንት (8) ሰዎች ከሶማሊ ክልል (የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው)  እንዲሁም ሶስት (3) ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው የድንበር ተሻጋሪ መኪና አሽከርካሪዎች ናቸው፡፡

የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተጋላጭነት ሁኔታቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው27
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው15
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው የታወቅጋር ግንኙነት የሌላቸው31
 ድምር73

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰባት (7) ሰዎች (4 ሰዎች ከደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል እና 1 ሰው ከአዲስ አበባ) ከበሽታው ያገገመ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ (159) ነው።

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ83,854
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ2844
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ73
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ489
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ1
አዲስ ያገገሙ7
በአጠቃላይ ያገገሙ159
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ5
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር655

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።   

  • መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
  • መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *