Categories
Amharic

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ሐምሌ -17, 2012

Categories
English

Notification Note on COVID-19 Situational Update July-24

Categories
Amharic

የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ ሐምሌ-16

Categories
English

Notification Note on COVID-19 Situational Update July-23

Categories
Amharic

ለ3ኛ ዙር የአደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ሰራተኞች የስራ ማብራሪያ ተሰጠ ሐምሌ-18

ሐምሌ 18 2012 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የአደጋ ማስተባባሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ የሆኑት አቶ አስቻለው አባይነህ በኢንስቲትዩቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኝተው ለ3ኛ ዙር የማዕከሉ አዲስ ገቢ ባለሙያዎች የስራ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አቶ አስቻለው የአደጋ ማስተባባሪያ ማዕከሉን ዓላማ ሲገልጹ በአለም አቀፍና እና በሃገር አቀፍ ደረጃ የጤና ስጋት ወይም አደጋ የሆነውን የኮሮና ቫይረስን ያለውን የሰው ሃይል፣ ገንዘብ፣ እውቀትን፣ መረጃንና ጊዜን አቀናጅቶ በመጠቀም ወቅቱን የጠበቀ ምላሽ በመስጠት በወረርሽኙ ምክንያት ሊደርስ የሚችለውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳትን ማስቆም ነው፡፡

አቶ አስቻለው በማብራሪያቸው የማዕከሉን መዋቅር፣ በመዋቅሩ ያሉ የስራ ክፍሎች የስራ ድርሻና ከእነሱ የሚጠበቁ ዝርዝር ተግባራት ምን እንደሆኑ ትኩረት ሰጥተው ገለጻ አድርገዋል፡፡

ሁሉም የማዕከሉ ሰራተኞች በኮሮና መከላከልና መቆጣጠር የተጣለባቸውን ሃላፊነት በትጋትና በቅንነት እንዲሰሩ አሳስበው፤ ስራቸውንም ሲሰሩ ለእራሳችውና ለቤተሰባቸው በሚል መንፈስ መሆን እንዳለበት አቶ አስቻለው አባይነህ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡