የአደጋ ጊዜ ሁኔታዎች

በአደጋ ጊዜ እንዴት እንዘጋጃለን?

የመቋቋም ዘዴ

በአስቸጋሪ ጊዜያት እና እንደዚህ ባሉ ወረርሽኞች ወቅት ሰዎች ቤት መቆየት፣ ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት፣   የመታመም እና የሚወዱትን ሰው በሞት የማጣት ፍራቻ፣ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተወሰዱት ሁኔታዎች እና እርምጃዎች አንድን  ሰው እንዲጨነቅ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ እንዴት እቅድ ማውጣት፣ ከበሽታ አስቀድሞ ውሳኔዎችን ማድረግ፣ ሕፃናትን እና በእኛ ጥበቃ ስር ያሉትን እንዴት እንደሚጠብቁ እና እንደሚደግፉ ማወቅ፣ ጭንቀትን ለመቋቋም መንገዶችን ማዘጋጀት እና መፈለግ  ያስፈለጋል፡፡

ጭንቀትን የመቋቋሚያ መንገዶች

  • መረጃዎችን ያግኙ
    • በእውቀት ላይ የተመሰረተ እርምጃዎችን በመውሰድ- በበሽታው ላይ ትክክለኛውን እና ወቅታዊ መረጃ ከታመነ ምንጭ ያግኙ፡፡
  • ግንኙነት ያርጉ
    • ከጎረቤቶቻችን ጋር፣ከምንወዳቸው ሰዎች  ጋር ጭንቀታችንን ለመቀነስ በመረጃ እና በዕለት ተዕለት ኑሮ መቋቋም ዘዴዎች ላይ ይነጋገሩ፣ ለሚወዷቸው ያካፍሉ፡፡እንደነዚህ ባሉ አስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ እርስ በእርሳችን እንዴት መረዳዳት እንደምንችል መማር አለብን፡፡

  • ይከላከሉ
    • ምንም እንኳን ቤት ቢሆኑም እንኳን በየቀኑ የመከላከያ ዘዴዎችን መተግበር ልማድዎ መሆን አለበት፡፡
  • ምልክቶችን ይከታተሉ
  • ቤትዎ ይቆዩ፤  አካላዊ ርቀትዎን ይጠብቁ

  • ገንዘብ፣ ምግብ እና የድንገተኛ ጊዜ አቅርቦቶችን ለመመደብ ዝግጁ ይሁኑ

የስነ-ልቦና ድጋፍ ለአረጋውያን

  • በዕድሜ የገፉ ሰዎች በተለይም የማስታወስ ችሎታቸው የቀነሰ ሰዎች የበለጠ ውጥረት፣ ቁጡ መሆን እና ጭንቀት ይታይባቸዋል፡፡ አረጋውያንን የሚንከባከቡ ከሆነ ምን ማድረግ የሚኖርብዎት ጥቃቄዎች፡-

    • እድሜቸው ገፋ ያሉ የማህበረሰባችን ክፍሎች ሊጠቀሙባቸው በሚችሉ ማስተማሪያ መንገዶች በኩል ስሜታዊ ድጋፍ መስጠት

    • ቀላል እና ግልፅ እውነታዎችን በመጠቀም ስለበሽታው ማስረዳት
    • አስፈላጊ ሲሆን መረጃውን መደጋገም
    • የመከላከያ እርምጃዎችን እንዲለማመዱ የሚያስፈልጋቸውን ግብአት ያቅርቡላቸው
    • ሌሎች የህክምና እክሎች ወይም የረጅም ጊዜ በሽታዎች እንደ ስኳር፣ ግፊት፣ የልብ ህመም ካለባቸው መድሀኒታቸውን ሳያቋርጡ የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቹ
    • ስለ በሽታው ምልክቶች፣ መተላፊያ መንገዶች፣ ለከባድ አደጋ ምክንያቶች፣ሕክምና እና የመልሶ ማገገም እድል እውነተኛ መረጃ ይስጡ
    • በቀላሉ ተደራሽ እና የታመኑ ሚዲያዎችን እንደ ስልኮች፣ሕዝባዊ ሚዲያዎች፣ቴሌቪዥን እና ሬዲዮዎች ይጠቀሙ፡፡
    • መመሪያዎችን በሚሰጡበት ጊዜ ግልፅ፣ አጭር፣ ያድርጉ እንዲሁም አክብሮት እና ትዕግሥት ያሳዩ
    • እንቅስቃሴን ለመጠበቅ፣ መሰልቸትን እና ጭንቀትን ለመቀነስ በቤት ውስጥ ለማከናወን ቀላል የሆኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያሳዩ አቸው

የስነ-ልቦና ድጋፍ ለአካል ጉዳተኞች

አካል ጉዳተኞች የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች በእንደዚህ አይነት ወረርሽኝ ወቅት እነሱን እና እነሱን ለሚንከባከቧቸው ሰዎች ተጨማሪ ጭንቀትን ያስከትላል፡፡

  • መልእክቶች ተደራሽ እና አግባብ መሆን አለባቸው

  • በገለልተኛ ቦታ እንክብካቤ እና ድጋፍ ለሚሹ አካል ጉዳተኞች ቀጣይ ድጋፍን ለማረጋገጥ ዕቅዶች መዘጋጀት አለባቸው
  • አካል ጉዳተኞች እና ተንከባካቢዎቻቸው በሁሉም የበሽታው ስርጭት መከላከል እና ምላሽ ደረጃዎች ውስጥ መካተት አለባቸው፡፡
  • ከአካል ጉዳተኞችና ከአካል ጉዳተኞች ማህበራት ጋር አጋርነት መጎልበት አለበት

COVID-19 እንዴት ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ይጨምራል?

  • ከበሽታው ጋር በተያያዘ የሚፈጠረው ጭንቀት፣ የማህበረሰብና የጥበቃ ትስስርና የማህበራዊ አገልግሎቶች መቀነስ (ትምህርት፣ ጤና ወዘተ) ስጋትን ይጨምራል፣
  • መራራቅ አንዱ ለዚህ ወረርሽኝ የመከላከያ ዘዴ ሲሆን እቤት ዉስጥ መዋልን ያበረታታል፤ በመሆኑም ለቤት ውስጥ ጥቃት ያጋልጣል (ለምሳሌ- የገቢ መቀነስና የውሳኔ ሰጪነት ሚና፤ የኃይል ሚዛኑ ለአንደኛዉ ፆታ ማጋደል፣
  • የሥነ-ተዋልዶ ጤና እና የፆታዊ ጥቃት ምላሽ አገልግሎት የመቀነስ ሁኔታና ሌሎች ተጓዳኝ አገልግሎቶች (ለምሳሌ፡ የማቆያ/shelters፣ የፍትሕ እርዳታ፤ ኢነንፎርሜሽን/መረጃ (hotlines) ማግኛና ሌሎች ሊስተጓጎሉ ይችላሉ፣

በዚህ ረገድ የጤናዉ ሥርዓት አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግና በCOVID-19 ወረርሽኝ ወቅትም ሴቶች አስፈለጊ ግልጋሎት ማግኘታቸዉን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ፡፡ ስለሆነም ማንኛዉም የዚህን ወረርሽኝን የመከላከል ሥራ ላይ ያሉ ባለ ድርሻ አካላት የፆታዊ ጥቃትን ጉዳይ ማወቅና በሴቶችና በሕፃናት ላይ ሊያሰከትል የሚችለዉን ጉዳት/ሰቆቃ ማወቅ፣ ማሳወቅና ግንዛቤ ማስጨበጥ እንዲሁም ምላሽ መስጠት ይጠበቅባቸዋል ፡፡

በተጨማሪም አብዛኛዉ የጤና ክብካቤ አገልግሎት ሰጪ ሴቶች በመሆናቸዉ በቤታቸውና በሥራ ቦታቸዉ ጥቃት ሊደርስባቸውና እዲሁም ወደ ሥራ ሲሄዱ ቤት ውሰጥ ጉዳት ደርሶ ሊያገኙ ስለሚችሉ የጤና አመራሮች ይህንን በመገንዘብ አስፈላጊ ዝግጅት (የደህንነት ቁሶች፤ የሥነ-ልቦና አገልግሎት ወዘተ…) በማድረግ ለሰራተኞቻቸው ተጨማሪ እገዛ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በወረርሽኝ ወቅት በሴቶች፣በሕጻናትና ልዩ ፍላጎት ባላቸው ማህበረሰቦች ላይ ለሚደርሰዉ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ለመቀነስና ምላሽ ለመስጠት ምን ይደረግ?

የስነ-ልቦና ድጋፍ ለልጆች

ልጆች በሚጨነቁበት ጊዜ መቃዠት እና ከተለመደው ባህሪያቸው የስሜት ለውጥ ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ የልጆች ባህሪዎች ብዙውን ጊዜ በሕይወታቸው ውስጥ ባሉ በአዋቂዎች ምላሽ ላይ የተመሰረተ ነው።

  • አዋቂዎች ልጆች እንዳይደነግጡ እና እንዳይረበሹ ስሜታቸውን መቆጣጠር እና መረጋጋት አለባቸው

  • የልጆችን ሀሳብ ልብ ብለው ያዳምጡ
  • ልጆች በአዋቂ ቁጥጥር ስር እንዲጫወቱ እና ዘና እንዲሉ እድሎችን ያዘጋጁ
  • ልጆች ከወላጆቻቸው ወይም ከአሳዳጊዎቻቸው ከተለዩ እንክብካቤ ሊሰጧቸው የሚችሉ ዘመዶች ኃላፊነት እንዲውስዱ ማድረግ እና ትኩረት ሰጥቶ መከታተል
  • እጃቸውን እንዴት እንደሚታጠቡ እና የመከላከያ መንገዶችን በጨዋታ መልክ ማሳየት
  • ቫይረሱን እና የመከላከያ ዘዴዎችን በተመለከተ አዝናኝ ጨዋታዎችን ያዘጋጁ
  • በልጆች ፊት ያልተረጋገጠ መረጃ አያውሩ
  • ለመከላከያ የሚጠቀሙበትን ቁሳቁሶችን ያቅርቡ

የስነ-ልቦና ድጋፍ በለይቶ ማቆያ እና በለይቶ ህክምና ለሚገኙ ሰዎች

  • ቀላል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ይስሩ

  • የመተንፈሻ አካላት እንቅስቃሴ ያድርጉ
  • መጽሃፎችን እና መጽሔቶችን ያንብቡ
  • በቴሌቪዥን የሚተላለፉ ስለ በሽታው አስፈሪ መልዕክቶችን በመመልከት የሚያሳልፉትን ጊዜ ይቀንሱ
  • ያለተረጋገጡ ወሬዎችን በማዳመጥ የሚያሳልፉትን ጊዜ ይቀንሱ
  • መረጃ ከታመኑ ምንጮች ያግኙ

የስነ-ልቦና ድጋፍ በሽታው ቁጥጥር እና ክትትል ስራ ላይ በቀጥታ ምላሽ እየሰጡ ለሚገኙ ሰዎች

  • አሁን ባለው ሁኔታ ውጥረት መሰማት በጣም የተለመደ ነው፡፡

  • ሠራተኞች በቂ የሆነ ሥራ እየሠሩ እንዳልሆኑ ሊሰማቸው ይችላል፣ ውጥረት ሥራዎን መሥራት እንደማይችሉ ወይም ደካማ እንደሆንዎ የሚያንፀባርቁ አይደሉም፡፡
  • መሠረታዊ ፍላጎቶችዎን ይንከባከቡ እና አጋዥ የመቋቋም ስልቶችን ይጠቀሙ በቂ እረፍት ይውሰዱ፣ በቂ እና ጤናማ ምግብ ይመገቡ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ እንዲሁም ከቤተሰብ እና ጓደኞች ጋር ያውሩ፡፡
  • እንደ ትንባሆ፣ አልኮሆል ወይም ሌሎች እጾች እነደ መቋቋሚያ ስልቶችን ከመጠቀም ይቆጠቡ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ልምዶችን ከባድ ጊዜን ለመቋቋም መጠቀም በረጅም ጊዜ አእምሯዊና አካላዊ ጤንነት መጓደል ያስከትላሉ።
  • የሚቻል ከሆነ በዲጂታል ዘዴዎች አማካይነት የሚወዷቸው ሰዎችን ያግኙ፡፡
  • ለማኅበራዊ ድጋፍ ባልደረቦችዎ፣ ሥራ አስኪያጅዎ ወይም ሌሎች የታመኑ ሰዎች ማህበራዊ ድጋፍ ያግኙ – የሥራ ባልደረቦችዎም ተመሳሳይ ልምዶች ሊኖሯቸው ይችላል፡፡
  • ለሚፈጠርቦት ጭንቀት ተጠያቂው እርስዎ እንዳልሆኑ ይወቁ፤ ሁሉም ሰው ይጨነቃል፤በተለየዩ ሁኔታዎች ችግሩን ይቋቋማል።

አግኙን

  • የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
  • ስዋዚላንድ መንገድ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
  • ስልክ: 0118276796
  • ኢሜል: ephieoc@gmail.com
  • ፖስታ፡ 1242

© 2012, የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ሙሉ መብት የተጠበቀ