Categories
Amharic

ዳግም ትኩረት ለኮቪድ-19

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ  ተይዘው  ህይወታቸውን የሚያጡ  ግለሰቦች  ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፡በትላንትናው እለት ብቻ 19 ሞት የተመዘገበ ሲሆን፤ 15ቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡በኢትዮጵያ ከመስከረም 12 ወዲህ በትላንትናው እለት የተመዘገበው የሞት  ቁጥር ከፍተኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ እስካሁን 2‚340 ግለሰቦች በኮቪድ -19 ህይወታቸውን አጥተዋል፤ ከእነዚህም ውስጥ 1‚716 ወይም (73%) ከአዲስ አበባ ከተማ ነው፡፡

በትላንትናው እለት 6‚659  ግለሰቦች ናሙና የሰጡ ሲሆን  ከዚህም  ውስጥ 935 ግለሰቦች   የኮቪድ -19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች  14 ግለሰቦች ወይም (14%) በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡  የኮቪድ -19 የስርጭት ምጣኔ በኢትዮጵያ ከጥር 28 እስከ ትላንትናው እለት ድረስ  ከ10% በላይ ሆኖ  ተመዝግቧል፤ በዚህም መሰረት ከ አፍሪካ  በኮቪድ -19 ከ10% በላይ የስርጭት ምጣኔ ከሚይስመዘግቡ ጥቂት ሀገራት ተርታ ኢትዮጵያን ያስመድባታል፡፡

በመሆኑም እያንዳንዱ ግለሰብ፤ ቤተሰብ፤ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ የሐይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ የጤና ባለሙያዎች፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተደጋግሞ የሚገለጹትን የመከላከያ መንገዶችን ማለትም  ማስክ ማድረግ፣ አዘውትሮ እጅን በሳሙና ና በውሃ በአግባቡ መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር በማፅዳት  እና አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ራሳቸውን ፣ ቤተሰቦቻቸውን እና ማህበረሰቡን ከበሽታው እንዲከላከሉ እና ሀላፊነታቸውን የኢትጵዮያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#COVID19Ethiopia

#NO MASK NO SERIVCE  

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *