Categories
Amharic

የፋሲካ እና የስቅለት በዓልን በማስመልከት የጤና ሚኒስቴር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ መልእክት አስተላለፉ።

የኮቪድ-19 ቫይረስ አሁንም አሳሳቢ መሆኑን እንደቀጠለ በሀገራችንም የላብራቶሪ ምርመራ ከሚደረግላቸው ሰዎች አኳያ በየቀኑ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ እንደሚያዙ እና በጽኑ ህክምና ክፍል ገብተው በከፋ ህመም እንደሚሰቃዩ፤በርካቶች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን እያጡ እንዳሉ እና የከፋ ጊዜ ላይ መድረሳችንን ገልፀዋል። አያይዘውም ሕብረተሰቡ የኮቪድ-19 የመከላከያ መንገዶችን ሳይዘናጋ እንዲተገብር እና የሚቆጣጠረውን አካል ሳይጠብቅ መተግበር ይኖርበታልም ብለዋል።

የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት መስፈርቱን የሚያሟሉ ዜጎች ሁሉ ክትባቱን ሊወስዱ እንደሚገባ እና ነገር ግን ክትባት የመከላከያ መንገዶችን የሚተካ ስላልሆነ የኮቪድ 19 መከላከያ መንገዶችን ለአፍታም ቢሆን ሳንዘናጋ መተግበር  እንደሚያስፈልግ ሚኒስተሯ አሳስበዋል።

በዚህ ሀይማኖታዊ በአል ላይ በእምነት ተቋማት መሰባሰቦች፤የመገበያያና የትራንስፖርት ቦታዎች ላይ መጨናናቆች ሊኖሩ ስለሚችሉ እየተስፋፋ ለመጣው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መባባስ ምክንያት ላለመሆን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ እንጠቀም፤ርቀታችንን እና የእጆቻችንን ንጽህና እንጠብቅ ሲሉ መልእክታቸውን አስተላለፈዋል፤በዓሉም የሰላም የደስታ እና የጤና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውንም ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል፡፡

#መልካምበዓል

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#COVID19Ethiopia #NOMASKNOSERIVCE  

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *