Categories
Amharic

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የመከላከል እና ምላሽ መስጠት ስራውን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማጠናከር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ ውይይት ተካሄደዋል

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሚኒስቴሮች ፣ የክልል ጤና ቢሮ ሀላፊዎች ፣ የብሔራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል-የኮቪድ-19 ምላሽ መስጫ ማዕከል እና ብሄራዊ የኮቪድ-19 ማስተባበሪያ ግብረ ሀይል አባላት ጋር በበየነ መረብ ባደረጉት ውይይት አሁን ያለውን የኮቪድ- 19 የስርጭት ሁኔታ እየተገበርነው ባለው የምላሽ አካሄድ መፍታት ስለማይቻል ምላሹን ከጤና ሴክተሩ ባለፈ ሁሉን አቀፍ ምላሽን ማጠናከር ፣ የአመራርና የህብረተሰቡን ትኩረትና ተሳትፎ ማሻሻል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ በውይይቱ ላይ ትኩረት መሰጠት ያለባቸውን ጉዳዮች አንስተዋል :-

* የኮቪድ -19 ስርጭት መቀልበስና የሞት መጠንን መቀነስ፣

* የዘርፈ ብዙ ምላሽን ማጠናከር፣

* የኮቪድ-19 ጽኑ ህክምና ተደራሽነት ማሳደግ፣

* የተቀናጀ  የግንዛቤ ማስጨበጫ እና  የህግ ማስከበር ንቅናቄዎችን ማከናወን፣

* የምርመራ ዓቅምና የክትባት ሽፋንን ማሳደግ ላይ ትኩረት በመስጠት ይሰራል ብለዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሚዲያ አካላት፣ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች፣ ከኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ህብረተሰቡን ማንቃትና ቫይረሱ እያስከተለ ያለዉን ጉዳት ማሳወቅ ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ እና በመመሪያ ቁጥር 30/2013 የተቀመጡ ህጎችን ተከታትሎ ማስፈጸምና የተቀመጡ ደንቦችን ሳያሟሉ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ላይ  አስፈላጊዉ  እርምጃ መዉሰድ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በተሰጡት መመሪያዎች መሰረት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከዚህ በፊት የኮቪድ-19 ቫይረስ በሀገራችን ከመከሰቱ በፊት የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን በመስራት ከተከሰተም በኋላ የተለያዩ የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። አሁንም ከወትሮው በበለጠ የኮቪድ-19 የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኮቪድ-19 ምላሽ ዋና አስተባባሪ አቶ አስቻለው አባይነህ ገልጸዋል።

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#COVID19Ethiopia

#NOMASKNOSERIVCE  

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *