Categories
Amharic

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ይገኛል

በትላንትናው ዕለት ለ5,916 ግለሰቦች የኮቪድ-19 ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን 511 ግለሰቦች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ይህ ማለት ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 9ቱ (9%) የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በኮቪድ-19 የመያዝ ምጣኔ ከ68 ቀናት በኋላ የመጀመሪያው ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

በኮቪድ-19 ቫይረስ ተይዘው ህይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦች ቁጥርም እየጨመረ ይገኛል። በትላንትናው ዕለት ብቻ 8 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ቫይረስ ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህ ቁጥር ከ47 ቀናት በኋላ ከፍተኛው የሞት ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ግለሰቦች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እያሻቀበ በአንድ ቀን ብቻ 25 ግለሰቦች ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የገቡ ሲሆን በአጠቃላይ 308 ግለሰቦች በአሁኑ ሰዓት በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥይገኛሉ። ከ53 ቀናት በኋላ ከፍተኛው ቁጥርም ሆኖ ተመዝግቧል።

አሁንም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ችላ ልንለው የሚገባ ጉዳይ አይደለም። የብዙዎችን ህይወት እየነጠቀ ብዙዎችን ደግሞ አካላዊ እና ማህበረሰባዊ ቀውስ ውስጥ እየከተተ ይገኛል። ስለሆነም እያንዳንዱ ግለሰብ ፣ ቤተሰብ ፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ የሐይማኖት ተቋማት ፣ ሲቪክ ማህበራት ፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣ የጤና ባለሙያዎች ፣ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ማስክ ማድረግ፣የእጅን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ እና ርቀትን በመጠበቅ በተጨማሪም የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ እነዚህን የኮቪድ-19 የመከላከያ መንገዶች የሚተገብሩ ከሆነ እራስዎን እና ቤተሰብዎን ከኮቪድ-19 ቫይረስ ተጋላጭነት ይቀንሳሉ ለወረርሽኙ መዛመትም ምክንያት አይሆኑም።

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

#COVID19Ethiopia

#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

#NOMASKNOSERIVCE  

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *