Categories
Amharic

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ መንገዶችን በአግባቡ ሊተገብር ይገባል።

በዕየለቱ የማስጠንቀቂያ መልክቶችን እያስተላለፍን ብንገኝም በህብረተሰቡ ዘንድ ባለው መዘናጋት እና የወረርሽኙ ስርጭት መጨመር ምክንያት በቫይረሱ የሚያዙ ፤ ህይወታቸውን የሚያጡ እና ወደ ፅኑ ህሙማን ህክምና ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል።

በትላንትናው ዕለት ለ7,686 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 985 ግለሰቦች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህ ማለት ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 13ቱ (13%) የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአንድ ቀን 19 ግለሰቦች ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የገቡ ሲሆን በአጠቃላይ 448 ግለሰቦች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ። 10 ግለሰቦች ደግሞ በትላንትናው ዕለት ህይወታቸውን አጥተዋል።

ስለሆነም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ፤ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፤ የሐይማኖት ተቋማት ፣ ሲቪክ ማህበራት ፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፤ የጤና ባለሙያዎች ፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የከፋ ችግር እንዳያስከትል በጋራ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥሪውን ያቀርባል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *