Categories
Amharic

የኮቪድ-19 ክትባትን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትና ለማሰራጨት እየተደረገ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ ውይይት ተደረገ

ከተለያዩ ተቋማት የተዋቀረው  ሀገራዊ የኮቪድ-19 ክትባት የበላይ አስተባባሪ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ክትባቱን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትና ለማሰራጨት እየተደረገ ያለውን አጠቃላይ  ዝግጅት ላይ ተወያይተዋል፡፡

የኮቪድ -19 ክትባት አቅርቦትና ስርጭት አስመልክቶ በታቀደው መሰረት የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራትና  ያለው ዝግጁነት በዝርዝር የቀርበ እና የተገመገመ ሲሆን ክትባቱ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ተደራሽ እንዲሆን በተቆጣጣሪ አካል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች፣ እንዲከተቡ የተለዩ አካለትን አስመልክቶና አስፈላጊውን ግንዛቤ ለማህበረሰቡ ለመፍጠር የተሰሩ ስራዎች ቀርቦ ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ በቀጣይ ትኩረት አግኝቶ ሊከናወኑ የሚገቡ ጉዳዮች ተለይቶ በጤና ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ  ታደሰ አቅጣጫ ተሰጥተዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የጤና ሚኒስትር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና  ኢንስቲቲዩት ፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አጄንሲና የተለያዩ የልማት አጋር ድርጅቶች ኃላፊዎችና ተወካዮች ተሳትፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *