Categories
Amharic

”የኮቪድ-19 ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የወጣው መመረያ ቁጥር 30/ 2013 የተቀመጡ የክልከላ እርምጃዎች ተግባራዊ በማያደርጉ አካላት ላይ እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲሁም ሌሎች ቅጣቶች እንደሚያስቀጣ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል”

የጤና ሚኒስቴር እና የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ  በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫውም  አሳሳቢ የሆነውን እና በፍጥነት እየተስፋፋ የሚገኘውን የኮቪድ-19 ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እና  ለመቆጣጠር የሚያግዝ መመሪያ ቁጥር 30 /2013 መውጣቱ ይታወሳል።ነገር ግን አተገባበሩ ላይ ከፍተኛ ክፍተት ይታያል። ስለሆነም በመመሪያው የተቀመጡ የክልከላ እርምጃዎችን ተከታትሎ ማስተግበር እና ማስፈፀም አስፈለጊ ነው ።

በመመሪያ 30/2013 የህግ አተገባበር ላይም:-

*ማንኛውም የኮቪድ-19 ቫይረስ ያለበት ግለሰብ ወደ ሃገር ውስጥ እንዳይገባ

*ቫይረሱ የተገኘበት ሰውም ወደ ማህበረሰቡ እንዳይቀላቀል

*በየትኛውም ቦታ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ሳያደርጉ መንቀሳቀስ

*የንግድና ሌሎች የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማስክ ያላደረገ ግለሰብን አገልግሎት እንዳይሰጡ ይህንን ጨምሮ ሌሎች የመመሪያ 30/2013 ዝርዝር ደንቦች ተግባራዊ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

መመሪያውን ተግባራዊ በማያደርጉ አካላት ላይም እስከ 3 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲሁም ሌሎች ቅጣቶች እንደሚያስቀጣ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል፡፡

ሊንኩን ተጭነው መመሪያ 30/2013 ማግኘት ይችላሉ::

https://covid19.ephi.gov.et/wp-content/uploads/2020/10/Registerd-COVID-19-Directive-2013_Final_051020.pdf #እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *