የኮቪድ – 19 ለመከላከል የሚውል የመጀመሪያው ዙር ክትባት ወደ ሀገር ውስጥ ኮቫክስ ከተሰኘው አለምአቀፍ ጥምረት 2.2 ሚሊዮን ዶዝ የፊታችን እሁድ በ28/06/2013 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ይገባል ። ክትባቱን ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰራ ይገኛል።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እየተስፋፋ ስለመጣ ሁሉም የማሕበረሰብ ክፍሎች ሳይዘናጉ የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብሩ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያሳስባል።