ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1560 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት (2) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መቶ ሰላሳ አምስት (135) ደርሷል፡፡ የላብራቶሪ ምርመራው የተደረገው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በብሄራዊ የእንስሳት ጤና በሽታዎች ምርመራ ማዕከል፣ በኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በደቡብ ብ/ብ/ህ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ላቦራቶሪ እና በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሜዲካል ማዕከል ላብራቶሪ የተከናወነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ስድስት (6) ሰዎች ከድሬዳዋ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ሰባ አምስት (75) ነው፡፡ የዛሬው ዕለት የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታም እንደሚከተለው ቀርቧል፣
ተ.ቁ | ዜግነት | መኖሪያ ቦታ | እድሜ | ፆታ | የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ | በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት |
1 | ኢትዮጲያዊ | ባቱ/ዝዋይ (አዲስ አበባ ህክምና በመከታተል ላይ ያለ) | 49 | ወንድ | የለውም | የለውም (በጤና ተቋም ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን ከተወሰደ ናሙና የተገኘ) |
2 | ኢትዮጲያዊ | ስልጢ ወረዳ፣ስልጤ ዞን፣ ደቡብ ክልል | 45 | ሴት | የላትም | የላትም (በቤት ለቤት ቅኝትና አሰሳ የተለየች) |
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 22,330 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 1560 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 2 |
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ | 55 |
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ | 0 |
አዲስ ያገገሙ | 6 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 75 |
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 3 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 135 |
የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ ከመተግበር መዘናጋት እንደሌለበት ጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጥብቅ ያሳስባሉ፡፡ ሕብረተሰቡ በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግና አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል እናሳስባለን፡፡
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ሚያዝያ 25፣ 2012 ዓ.ም