ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2424 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ አንድ (11) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ ስልሳ አንድ (261) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያዊያን እድሜያቸው ከ19-47 ዓመት የሆኑ ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 8 ሰዎች ከአፋር ክልል (ሰመራ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል (መቐለ ለይቶ ማቆያ)፣ 1 ሰው ከሶማሌ ክልል (ጂግጅጋ ለይቶ ማቆያ) እና 1 ሰው ከአማራ ክልል (ሰሜን ሸዋ ዞነ አጣዬ ከተማ ለይቶ ማቆያ) ይገኛሉ።
የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የተጋላጭነት ሁኔታ | የታማሚዎች ቁጥር |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው | 11 |
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው | 0 |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው | 0 |
ድምር | 11 |
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አንድ (1) ሰው ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገመ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ስድስት (106) ነው።
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 39,048 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 2424 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 11 |
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ | 148 |
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ | 0 |
አዲስ ያገገሙ | 1 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 106 |
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 5 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 261 |
የዕለቱ የላብራቶሪ ምርመራ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ ኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በአማራ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት (ባህር ዳር እና ደሴ)፣ በደቡብ ብ/ብ/ሕ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ አፋር ክልላዊ ላብራቶሪ፣ በነቀምት የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በደብረብርሃን አጠቃላይ ሆስፒታል፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላብራቶሪ፣ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ፣ በአርሲ ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ፣ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ እና በጅማ ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ሴንተር የተከናወነ ነው፡፡
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።
- መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
- መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
- መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
- መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ግንቦት 4፣ 2012 ዓ.ም