ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1764 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ አንድ (11) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ ሃምሳ (250) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ 10 ወንድ እና 1 ሴት እንዲሁም እድሜያቸው ከ18 – 38 ዓመት የሆኑ ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 5 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል (ትግራይ ለይቶ ማቆያ)፣ 3 ሰዎች ከአፋር ክልል (አፋር ለይቶ ማቆያ) እና 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል (አዳማ ለይቶ መከታተያ) ይገኛሉ።
የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የተጋላጭነት ሁኔታ | የታማሚዎች ቁጥር |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው | 5 |
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው | 6 |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው | 0 |
ድምር | 11 |
- በዚህ ሪፖርት ከትግራይ ክልል የተካተቱት ሁለት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች በትላንትናው ዕለት በክልሉ ሪፖርት የተደረጉ ናቸው።
የላብራቶሪ ምርመራው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በአርማውር ሃንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጲያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በአማራ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት (ባህር ዳር) ፣ በአፋር ክልል ላብራቶሪ፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላብራቶሪ፣ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ የተከናወነ ነው፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ስድስት (6) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ አምስት (105) ነው።
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 36,624 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 1764 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 11 |
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ | 138 |
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ | 0 |
አዲስ ያገገሙ | 6 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 105 |
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 5 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 250 |
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ ከሰዎች ጋር ሊኖረን የሚችሉ ግንኙነቶችን በመገደብ እና ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ መገኘታችን አስገዳጅ በሚሆንበት ሁኔታ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግ ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ግንቦት 3፣ 2012 ዓ.ም