ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1861 የላብራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መቶ ዘጠና አራት(194) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ሲሆኑ እድሜያቸው ከ23-33 ዓመት የሆኑ ይገኙበታል። የሁሉም ታማሚዎች የመኖሪያ ቦታ አዲስ አበባ ነው።
የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የተጋላጭነት ሁኔታ | የታማሚዎች ቁጥር |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው | 0 |
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው | 2 |
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት በመጣራት ላይ ያለ | 1 |
ድምር | 3 |
የላብራቶሪ ምርመራው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በአርማውር ሃንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጲያ ባዮተክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በነቀምት የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በአማረ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላብራቶሪ፣ በአርሲ ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ፣ በጎንደር ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ የተከናወነ ነው፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሁለት (2) ሰዎች (1 ከአዲስ አበባ እና 1 ከኦሮሚያ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና አምስት (95) ነው።
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 30,306 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 1,861 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 3 |
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ | 93 |
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ | 1 |
አዲስ ያገገሙ | 2 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 95 |
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 4 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 194 |
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን የዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ ከሰዎች ጋር ሊኖረን የሚችሉ ግንኙነቶችን በመገደብ እና ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ መገኘታችን አስገዳጅ በሚሆንበት ሁኔታ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግ ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ሚያዝያ 30፣ 2012 ዓ.ም