ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4675 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አርባ አንድ (141) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5175 ደርሷል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 81 ወንድ እና 60 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 2 ወር እስከ 87 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት አንድ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሁለት ሰዎች የውጭ ሃገር ዜጋ ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 113 ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ 15 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 6 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል፣ 2 ሰዎች ከሶማሊ ክልል፣ 1 ሰው ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና 1 ሰው ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ናቸው።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (4 ከጤና ተቋም እና 14 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኝበት ናሙና የለም። ከዚህ ባለፈ ሶስት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰማንያ አንድ (81) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከለው ቀርቧል፡፡
ተ.ቁ | የመኖሪያ አድራሻ | ጾታ | ዕድሜ | ማብራሪያ |
1 | አዲስ አበባ | ወንድ | 52 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ |
2 | አዲስ አበባ | ወንድ | 72 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ |
3 | አዲስ አበባ | ሴት | 62 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ |
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሃምሳ ስምንት (58) ሰዎች (44 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ እና 1 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1544 ነው።
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 232,050 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 4675 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 141 |
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው | 3,548 |
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር | 30 |
አዲስ ያገገሙ | 58 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 1,544 |
በዕለቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች | 3 |
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 81 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 5,175 |
የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም