Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ሰኔ-17

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4034 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት (186) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5034 ደርሷል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 73 ወንድ እና 113 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 6 ወር እስከ 75 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት አንድ መቶ ሰማያ አንድ ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አምስት ሰዎች የውጭ ሃገር ዜጋ ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 147 ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ 16 ሰዎች ከሶማሊ ክልል፣ 10 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 8 ሰዎች ከድሬድዋ ከተማ አስተዳደር፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ እና 1 ሰው ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 35 (15 ከጤና ተቋም እና 20 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን ሁለት  ናሙናዎች ከጤና ተቋም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበቸዋል። በተጨማሪ አንድ በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበር ሰው ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ ስምንት (78) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡  ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከለው ቀርቧል፡፡

ተ.ቁየመኖሪያ አድራሻጾታዕድሜማብራሪያ
1አዲስ አበባወንድ38በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ
2ሶማሊሴት19በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበረች
3ሶማሊሴት40በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበረች

የሚኒስቴሮች ኮሚቴ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል፤ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አዋጂን ለማስፈፀም የሚያስችል መመሪያ ተግባራዊ እንዲደረግ ወስኗል፡፡ በዚህም መሠረት በመመሪያው ውስጥ የተቀመጡ_ሁሉንም መስፈርቶችን_የሚያሟሉ-ሰዎች በቤትውስጥ ሆነው የሕክምና ክትትል ማድረግ_ይችላሉ። ስለሆነም በቤት ውስጥ ሆነው የኮሮና ቫይረስ ሕክምና የሚያገኙ ሰዎች በሽታው ወደ ሌሎች የቤተሰብ አባላት እንዳይሰራጭ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግ እንዳለባቸው ማስገንንዘብ  እንወዳለን።

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰባ አራት (74) ሰዎች (63 ከአዲስ አበባ፣ 6 ከትግራይ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ እና 1 ሐረሪ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1486 ነው።

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ227,375
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ4034
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ186
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው3,468
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር38
አዲስ ያገገሙ74
በአጠቃላይ ያገገሙ1,486
በዕለቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች3
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ78
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር5,034

በየዕለቱ የሚቀርበው የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን የተመለከተ መግለጫ ከሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በhttp://covid19.et ላይ የሚገኝ የሚሆን ይሆናል።

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *