ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3775 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰማንያ አምስት (185) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4848 ደርሷል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 47 ወንድ እና 138 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 3 ወር እስከ 80 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት አንድ መቶ ሰማንያ አራት (184) ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንድ ሰው የውጭ ሃገር ዜጋ ነው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 160 ሰዎች ከአዲስ አበባ (105 ሰዎች ተመላሾች እና በ ማቆያ የነበሩ) ፣ 7 ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ 7 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ከሶማሊ ክልል፣ 2 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል፣ 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል እና 1 ሰው ከሐረሪ ክልል ናቸው።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 30 (11 ከጤና ተቋም እና 19 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም።
የሚኒስቴሮች ኮሚቴ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል፤ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አዋጂን ለማስፈፀም የሚያስችል መመሪያ ተግባራዊ እንዲደረግ ወስኗል፡፡ በዚህም መሠረት በመመሪያው ውስጥ የተቀመጡ_ሁሉንም መስፈርቶችን_የሚያሟሉ-ሰዎች በቤትውስጥ ሆነው የሕክምና ክትትል ማድረግ_ይችላሉ። ስለሆነም በቤት ውስጥ ሆነው የኮሮና ቫይረስ ሕክምና የሚያገኙ ሰዎች በሽታው ወደ ሌሎች የቤተሰብ አባላት እንዳይሰራጭ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግ እንዳለባቸው ማስገንንዘብ እንወዳለን።
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አንድ መቶ አስራ አምስት (115) ሰዎች (81 ከአዲስ አበባ፣ 23 ከአማራ ክልል፣ 6 ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ከሐረሪ ክልል፣ 2 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና 1 ትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1412 ነው።
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 223,341 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 3775 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 185 |
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው | 3,359 |
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር | 38 |
አዲስ ያገገሙ | 115 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 1,412 |
በዕለቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች | 0 |
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 75 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 4,848 |
በየዕለቱ የሚቀርበው የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን የተመለከተ መግለጫ ከሰኔ 18 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በhttp://covid19.et ላይ የሚገኝ የሚሆን ይሆናል።
የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም