Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ግንቦት-2

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2171 የላብራቶሪ ምርመራ ሀያ ዘጠኝ (29) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ (239) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ  እድሜያቸው ከ15 – 45 ዓመት የሆኑ ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 21 ሰዎች ከአዲስ አበባ  ሲሆኑ፣ 7 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ሶማሌ ለይቶ ማቆያ) እና 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል (አዳማ ከተማ በቤት ለቤት አሰሳ እና ቅኝት የተለየ) ይገኛሉ።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተጋላጭነት ሁኔታየታማሚዎች ቁጥር
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው8
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው21
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው0
 ድምር29

የላብራቶሪ ምርመራው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በብሄራዊ የእንስሳት ጤና በሽታዎች ምርመራ ማዕከል፣ በኢትዮጲያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በነቀምት የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በአማራ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት (ባህር ዳር እና ደሴ) ፣ በጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ በደብረብርሀን አጠቃላይ ሆስፒታል፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላብራቶሪ፣ በጦር ሀይሎች አጠቃላይ ሆስፒታል፣ በአርሲ ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ፣ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ፣ በጅማ ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ሴንተር እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ  የተከናወነ ነው፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሁለት (2) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና ዘጠኝ (99) ነው።

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ34,860
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ2171
በዛሬው  ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ29
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ133
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ0
አዲስ ያገገሙ2
በአጠቃላይ ያገገሙ99
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ5
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር239

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ ከሰዎች ጋር ሊኖረን የሚችሉ ግንኙነቶችን በመገደብ እና ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ መገኘታችን አስገዳጅ በሚሆንበት ሁኔታ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግ ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።  

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 2፣ 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *