Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ሰኔ-12

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4809 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አስራ ስድስት (116) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4070 ደርሷል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 76 ወንድ እና 40 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 3 እስከ 78 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ሰዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 101 ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ 6 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል፣  1 ሰው ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና 1 ሰው ከአፋር ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 37 (24 ከጤና ተቋም እና 13 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን አንድ ናሙና ከጤና ተቋም እና አንድ ናሙና ከማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በተጨማሪ አምስት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ ሁለት (72) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡  ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከለው ቀርቧል፡፡

ተ.ቁየመኖሪያ አድራሻጾታዕድሜማብራሪያ
1ሶማሊ ክልልወንድ70በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ
2አዲስ አበባወንድ68በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ
3አዲስ አበባወንድ45በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ
4ድሬዳዋሴት70በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ
5ሐረሪ ክልልወንድ4 ወርበህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ
6አዲስ አበባወንድ85በጤና ተቋም ላይ የነበሩ
7አዲስ አበባሴት40አስክሬን ምርመራ ላይ ቫይረሱ የተገኘ

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ዘጠና ሶስት (93) ሰዎች (88 ከአዲስ አበባ፣ 2 ከአማራ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል እና 1 ሰው ከኦሮሚያ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1027 ነው።

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ                                   

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ207,023
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ4,809
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ116
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው2,969
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር32
አዲስ ያገገሙ93
በአጠቃላይ ያገገሙ1,027
በዕለቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች7
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ72
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር4,070

በአሁኑ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ በሽታ በሕብረተሰቡ ውስጥ የተሰራጨ በመሆኑ ማንኛውንም የቀብር ስነስርዓት ውስን የቤተሰብ አባላት በተገኙበት በጥንቃቄ በመፈጸም ሊፈጠር የሚችለውን የሰው መሳባሰብ በማስቀረት የበሽታውን ስርጭት እንግታ፤ ተጨመሪ ሰው በእኛ ምክንያት በቫይረሱ እንዳይያዝ የበኩላችንን እንወጣ!

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ሰኔ 12 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *