ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4853 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ዘጠና አምስት (195) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3954 ደርሷል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 90 ወንድ እና 105 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 1 እስከ 85 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ሰዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 144 ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ 12 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 12 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 7 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 7 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ 4 ሰዎች ከሶማሊ ክልል፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል እና 2 ሰዎች ከሐረሪ ክልል ናቸው።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 44 (19 ከጤና ተቋም እና 25 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም። ከዚህ ባለፈ ሁለት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰልሳ አምስት (65) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከለው ቀርቧል፡፡
ተ.ቁ | የመኖሪያ አድራሻ | ጾታ | ዕድሜ | ማብራሪያ |
1 | አዲስ አበባ | ወንድ | 80 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ |
2 | አዲስ አበባ | ሴት | 60 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ |
በአሁኑ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ በሽታ በሕብረተሰቡ ውስጥ የተሰራጨ በመሆኑ ማንኛውንም የቀብር ስነ–ስርዓት ውስን የቤተሰብ አባላት በተገኙበት በጥንቃቄ በመፈጸም ሊፈጠር የሚችለውን የሰው መሳባሰብ በማስቀረት የበሽታውን ስርጭት እንግታ፤ ተጨመሪ ሰው በእኛ ምክንያት በቫይረሱ እንዳይያዝ የበኩላችንን እንወጣ!
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች (73 ከአዲስ አበባ፣ 5 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአማራ ክልል እና 2 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 934 ነው።
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 202,214 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 4,853 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 195 |
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው | 2,953 |
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር | 27 |
አዲስ ያገገሙ | 85 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 934 |
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 65 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 3,954 |
የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ሰኔ 11 ቀን 2012 ዓ.ም