ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5274 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃያ ዘጠኝ (129) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3759 ደርሷል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 79 ወንድ እና 50 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 1 እስከ 70 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ሰዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 85 ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ 11 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 10 ሰዎች ከሶማሊ ክልል፣ 7 ሰዎች ከድ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ 6 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና 1 ሰው ከአፋር ክልል ናቸው።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (11 ከጤና ተቋም እና 7 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም። ከዚህ ባለፈ ሁለት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ ሶስት (63) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከለው ቀርቧል፡፡
ተ.ቁ | የመኖሪያ አድራሻ | ጾታ | ዕድሜ | ማብራሪያ |
1 | ድሬድዋ | ወንድ | 60 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ |
2 | አዲስ አበባ | ወንድ | 30 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ |
በአሁኑ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ በሽታ በሕብረተሰቡ ውስጥ የተሰራጨ በመሆኑ ማንኛውንም የቀብር ስነ–ስርዓት ውስን የቤተሰብ አባላት በተገኙበት በጥንቃቄ በመፈጸም ሊፈጠር የሚችለውን የሰው መሳባሰብ በማስቀረት የበሽታውን ስርጭት እንግታ፤ ተጨመሪ ሰው በእኛ ምክንያት በቫይረሱ እንዳይያዝ የበኩላችንን እንወጣ!
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አንድ መቶ አስራ አንድ (111) ሰዎች (109 ከአዲስ አበባ እና 2 ከድሬዳዋ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 849 ነው።
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 197,361 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 5,274 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 129 |
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው | 2,845 |
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር | 30 |
አዲስ ያገገሙ | 111 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 849 |
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 63 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 3,759 |
የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ሰኔ 10 ቀን 2012 ዓ.ም