ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5102 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ዘጠኝ (109) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3630 ደርሷል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 60 ወንድ እና 49 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 1 እስከ 78 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ሰዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 81 ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ 9 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከሶማሊ ክልል, 4 ሰዎች ከ ደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ 3 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 3 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 3 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ እና 2 ሰዎች ከሐረሪ ክልል ናቸው።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 20 (5 ከጤና ተቋም እና 15 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የ45 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበበ ነዋሪ ሴት ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ-አንድ (61) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡
በአሁኑ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ በሽታ በሕብረተሰቡ ውስጥ የተሰራጨ በመሆኑ ማንኛውንም የቀብር ስነ–ስርዓት ውስን የቤተሰብ አባላት በተገኙበት በጥንቃቄ በመፈጸም ሊፈጠር የሚችለውን የሰው መሳባሰብ በማስቀረት የበሽታውን ስርጭት እንግታ፤ ተጨመሪ ሰው በእኛ ምክንያት በቫይረሱ እንዳይያዝ የበኩላችንን እንወጣ!
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አንድ መቶ አስራ ስምንት (118) ሰዎች (115 ከአዲስ አበባ እና 3 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 738 ነው።
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 192,087 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 5,102 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 109 |
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው | 2,829 |
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር | 32 |
አዲስ ያገገሙ | 118 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 738 |
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 61 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 3,630 |
የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ.ም