ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5636 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰባ ስድስት (176) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3521 ደርሷል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 116 ወንድ እና 60 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 5 እስከ 90 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት አንድ መቶ ሰባ አምስት (175) ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንድ (1) ሰው የውጭ ሃገር ዜጋ ነው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 98 ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ 33 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 31 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 7 ሰዎች ከሶማሊ ክልል፣ 3 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና 2 ሰዎች ከአፋር ክልል ናቸው።
ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 28 (17 ከጤና ተቋም እና 11 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን አንድ ናሙና ከጤና ተቋም የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። በተጨማሪ ሁለት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ (60) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከለው ቀርቧል፡፡
ተ.ቁ | የመኖሪያ አድራሻ | ጾታ | ዕድሜ | ማብራሪያ |
1 | አማራ ክልል | ወንድ | 60 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ |
2 | አዲስ አበባ | ወንድ | 19 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ |
3 | አማራ ክልል | ወንድ | 32 | አስክሬን ምርመራ ላይ ቫይረሱ የተገኘ |
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰባ አምስት (75) ሰዎች (31 ከአዲስ አበባ፣ 28 ከሶማሊ ክልል፣ 10 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአማራ ክልል እና 1 ከአፋር ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 620 ነው።
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 186,985 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 5,636 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 176 |
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው | 2,839 |
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር | 29 |
አዲስ ያገገሙ | 75 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 620 |
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 60 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 3,521 |
በአሁኑ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ በሽታ በሕብረተሰቡ ውስጥ የተሰራጨ በመሆኑ ማንኛውንም የቀብር ስነ–ስርዓት ውስን የቤተሰብ አባላት በተገኙበት በጥንቃቄ በመፈጸም ሊፈጠር የሚችለውን የሰው መሳባሰብ በማስቀረት የበሽታውን ስርጭት እንግታ፤ ተጨመሪ ሰው በእኛ ምክንያት በቫይረሱ እንዳይያዝ የበኩላችንን እንወጣ!
የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ም