Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ሰኔ-7

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4845 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰባ ዘጠኝ (179) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3345 ደርሷል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 116 ወንድ እና 63 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ ሁለት ወር እስከ 80 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት አንድ መቶ ሰባ ስድስት (176) ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሶስት (3) ሰዎች የውጭ ሃገር ዜጎች ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 111 ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ 23 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 15 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 11 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 9 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 5 ሰዎች ከሶማሊ ክልል፣ 2 ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ 2 ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና 1 ሰው ከሐረሪ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 30 (24 ከጤና ተቋም እና 6 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን በሁለት ናሙናዎች (1 ከጤና ተቋም እና 1 ከማህበረሰብ) የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ሁለቱም የአዲስ አበባ ነዋሪ የነበሩ ሴትና ወንድ ኢትዮጵያውያን ናቸው። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሀምሳ ሰባት (57) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሃምሳ (50) ሰዎች (41 ከአዲስ አበባ፣ 4 ከአማራ ክልል፣ 3 ከአፋር ክልል እና 2 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 545 ነው።

በሕብረተሰቡ ውስጥ ባለው የቫይረስ ስርጭት ምክንያት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነው። በመሆኑም እኛ ወይም የምንወደው ሰው ቀጥሎ በቫይረሱ የሚያዘው ሰው ልንሆን እንደሚችል በመገንዘብ ከመቼውም ግዜ በላይ በመጠንቀቅ ስርጭቱን ማቆም እንችላለን። በዚህ ወረርሽኝ አንዳችን ለአንዳችን ዘብ በመቆም የኮሮና ቫይረስ የመከላከያ ዘዴዎችን ለመተግበር አንዳችን ስንዘናጋ ሌላችን ካስታወስን ህይወት ልናተርፍ እንችላለን። በመሆኑም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን አንዱን ዘዴ ከሌላው ሳናማርጥ በሙሉ መተግበር ይገባናል።

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ181349
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ4845
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ179
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው2741
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር30
አዲስ ያገገሙ50
በአጠቃላይ ያገገሙ545
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ57
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር3345

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ሰኔ 7 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *