ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5709 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት መቶ አርባ አምስት (245) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2915 ደርሷል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 172 ወንድ እና 73 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 1 እስከ 85 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁለት መቶ አርባ አንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አራቱ የውጭ ሃገር ዜጎች ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ ዘጠና (190) ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ አስራ ሰባት (17) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ አስራ ስድስት (16) ሰዎች ከሶማሊ ክልል ፣ አስራ አምስት (15) ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ አራት (4) ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል እንዲሁም ሶስት (3) ሰዎች ከአማራ ክልል ናቸው።
በሕብረተሰቡ ውስጥ ባለው የቫይረስ ስርጭት ምክንያት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነው። በመሆኑም እኛ ወይም የምንወደው ሰው ቀጥሎ በቫይረሱ የሚያዘው ሰው ልንሆን እንደሚችል በመገንዘብ ከመቼውም ግዜ በላይ በመጠንቀቅ ስርጭቱን ማቆም እንችላለን። በዚህ ወረርሽኝ አንዳችን ለአንዳችን ዘብ በመቆም የኮሮና ቫይረስ የመከላከያ ዘዴዎችን ለመተግበር አንዳችን ስንዘናጋ ሌላችን ካስታወስን ህይወት ልናተርፍ እንችላለን። በመሆኑም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን አንዱን ዘዴ ከሌላው ሳናማርጥ በሙሉ መተግበር ይገባናል።
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሰባት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አርባ ሰባት (47) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከለው ቀርቧል፡፡
ተ.ቁ | የመኖሪያ አድራሻ | ጾታ | ዕድሜ | ማብራሪያ |
1 | አዲስ አበባ | ወንድ | 75 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ |
2 | አዲስ አበባ | ሴት | 70 | በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ |
3 | አዲስ አበባ | ወንድ | 80 | በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ |
4 | አዲስ አበባ | ሴት | 29 | በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ |
5 | አዲስ አበባ | ወንድ | 48 | በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ |
6 | አዲስ አበባ | ሴት | 85 | በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ |
7 | አዲስ አበባ | ሴት | 21 | በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ |
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ ሰባት (17) ሰዎች (16 ከአዲስ አበባ እና 1 ከደ/ብ/ብ/ህ ክልል ትላንት በክልሉ ሪፖርት የተደረገ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 451 ነው።
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 170,860 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 5709 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 245 |
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው | 2415 |
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር | 38 |
አዲስ ያገገሙ | 17 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 451 |
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 47 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 2915 |
የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓ.ም