Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ሰኔ-3

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6187 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰባ (170) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2506 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 93 ወንድ እና 77 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 2 እስከ 115 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰማንያ አንድ (81) ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ ሃምሳ ሰባት (57) ሰዎች ከሶማሊ ክልል ፣ አስራ ሶስት (13) ሰዎች ከአማራ ክልል፣ ሰባት (7) ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ ሰባት (7) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ ሶስት (3) ሰዎች ከሐረሪ ክልል እንዲሁም ሁለት (2) ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል ናቸው።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሶስት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። የመጀመርያ የ115 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፣ ሁለተኛ የ35 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ እና ሶስተኛ የ84 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ ሁሉም ህይወታቸው አልፎ ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል በተደረገ ምርምራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰላሳ አምስት (35) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡ 

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሃያ ሁለት (22) ሰዎች ከአዲስ አበባ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 401 ነው።

የኮሮና ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ በቁጥር ከሚገለጸው በላይ ነው፡፡ ከእያንዳንዱ በየእለቱ ከምንገልጻቸው በቫይረሱ ከተያዙ ቁጥሮች ጀርባ የብዙ ቤተሰቦች እና ጓደኞቻቸው ጭንቀት እና ስጋት አለ፡፡

እርስዎም በዚህ ወቅት ቤተሰብ ባለመጠየቅዎ፣ ለቅሶ ባለመድረስዎ፣ ሰርግ ባለመታደምዎ፣ የወለዱ ጓደኞችዎን ወይም ዘመድዎን ባለመጠየቅዎ ወይም ከሚዎዷቸው ጋር ረፍትዎን አብረው ባለማሳለፍዎ ተጨንቀው እና አዝነው ይሆናል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ስለ ራስዎ፣ ስለሚዎዳቸው ብለውና ሕይወት ከኮቪድ-19 በኋላ በነጻነት እንደሚቀጥል በመረዳትዎ ስለሆነ አስተዋይ በመሆንዎ ሊበራታቱ ይገባዎታል፤ ሁሉም የሚጠበቅበትን በኃላፊነት በመወጣት ሊከሰት የሚችለውን የሕመም እና ሞት እንከላከል፡፡

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ158,521
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ6,187
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ170
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው2,068
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር33
አዲስ ያገገሙ22
በአጠቃላይ ያገገሙ401
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ35
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር2,506

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *