ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1382 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ ሰባት (17) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መቶ ስልሳ ሁለት (162) ደርሷል፡፡ የላብራቶሪ ምርመራው የተደረገው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በአርማውር ሃንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ ኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በአማራ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት (ባህር ዳር እና ደሴ)፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላብራቶሪ፣ በአርሲ ዩኒቨርስቲ ላቦራቶሪ፣ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ እና በጅማ ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ማዕከል የተከናወነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሁለት (2) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና ሶስት (93) ነው። የዕለቱ ታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታም እንደሚከተለው ቀርቧል፣
ተ.ቁ | ዜግነት | መኖሪያ ቦታ | እድሜ | ፆታ | የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ | በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት |
1 | ኢትዮጵያዊ | አዲስ አበባ | 27 | ወንድ | የለውም | የስራው ባህሪ ተጋላጭነት ያለው |
2 | ኢትዮጵያዊ | 20 | ወንድ | ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – | |
3 | ኢትዮጵያዊ | 25 | ወንድ | ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – | |
4 | ኢትዮጵያዊ | 14 | ወንድ | ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – | |
5 | ኢትዮጵያዊ | 26 | ወንድ | ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – | |
6 | ኢትዮጵያዊ | 65 | ወንድ | ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – | |
7 | ኢትዮጵያዊ | አዲስ አበባ | 28 | ሴት | የላትም | ያላት |
8 | ኢትዮጵያዊ | አፋር (የተገኝው አዲስ አበባ) | 39 | ወንድ | የለውም | በመጣራት ላይ ያለ |
9 | ኢትዮጵያዊ | 50 | ወንድ | ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – | |
10 | ኢትዮጵያዊ | 30 | ወንድ | ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – | |
11 | ኢትዮጵያዊ | አዲስ አበባ | 53 | ሴት | የላቻውም | ያላቸው |
12 | ኢትዮጵያዊ | 23 | ወንድ | ከሶማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – | |
13 | ኢትዮጵያዊ | 24 | ወንድ | ከሶማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – | |
14 | ኢትዮጵያዊ | 27 | ወንድ | ከሶማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – | |
15 | ኢትዮጵያዊ | 20 | ወንድ | ከሶማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – | |
16 | ኢትዮጵያዊ | 22 | ወንድ | ከሶማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – | |
17 | ኢትዮጵያዊ | 41 | ወንድ | ከሶማሊያ የተመለሰና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | – |
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 26,517 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 1,382 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 17 |
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ | 63 |
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ | 0 |
አዲስ ያገገሙ | 2 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 93 |
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 4 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 162 |
የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ ከመተግበር መዘናጋት እንደሌለበት ጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጥብቅ ያሳስባሉ፡፡ ሕብረተሰቡ በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግና አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል እናሳስባለን፡፡
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ሚያዝያ 28፣ 2012 ዓ.ም