ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6092 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ ስድስት (86) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2020 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 51 ወንድ እና 35 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 7 እስከ 82 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ስልሳ ስድስት (66) ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ሰባት (7) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ ሰባት (7) ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ አራት (4) ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ አንድ (1) ሰው ከአማራ ክልል እንዲሁም አንድ (1) ሰው ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ናቸው።
ከዚህ ቀደም በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ እያለች በሰላም እንደተገላገለች የተገለፀችውን እናት ጨምሮ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሰባት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሀያ ሰባት (27) ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡
ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ እንደሚከለው ቀርቧል፡፡
ተ.ቁ | የመኖሪያ አድራሻ | ጾታ | ዕድሜ | ማብራሪያ |
1 | አዲስ አበባ | ሴት | 34 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረች |
2 | አዲስ አበባ | ወንድ | 56 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ |
3 | አዲስ አበባ | ወንድ | 55 | በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ |
4 | ኦሮሚያ | ወንድ | 36 | በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ |
5 | አዲስ አበባ | ሴት | 65 | በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ |
6 | አዲስ አበባ | ሴት | 33 | በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ |
7 | አዲስ አበባ | ሴት | 26 | በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ የተገኘ |
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ስልሳ ሶስት (63) ሰዎች (46 ከአዲስ አበባ፣13 ከሶማሊ ክልል፣ 3 ከኦሮሚያ ክልል እና 1 ከአማራ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 344 ነው።
የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡
- በሀገራችን ባለፉት 7 ቀናት ብቻ 848 ሰዎች በቫይረሱ እንደተያዙ እንዲሁም 16 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ሕይዎታቸው ማለፉ ተረጋግጧል፤
- ነገር ግን በሕብረተሰቡ ዘንድ በሽታውን ለመከላከል የሚረዱ የመከላከያ ዘዴዎችን ከመተግበር አኳያ እጅግ ብዙ ክፍተቶች እየተስተዋሉ ነው፡፡
- ስለሆነም ሁሉም የሕብረተሰብ አካል፣ ክልሎች፣ የከተማ አስተዳደሮች እና የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች እንዲሁም ሌሎች አካላት የበሽታው ስርጭት ተሰፋፍቶ ከአቅም በላይ ከመድረሱና ለከፋ ችግር ከመዳረጋችን በፊት የጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ከምንጊዜውም በላይ ሕብረተሰቡን ባማከለና ባሳተፈ መልኩ አስፈላጊውን የመከላከል ሥራ እንዲተገብሩ በአጽንኦት እናሳስባለን!!
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 142960 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 6092 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 86 |
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው | 1647 |
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር | 32 |
አዲስ ያገገሙ | 63 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 344 |
በአጠቃላይ በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 27 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 2020 |
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም