Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ግንቦት-28

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5798 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ስልሳ ዘጠኝ (169) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1805 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 111 ወንድ እና 58 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 1 እስከ 78 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት መቶ ስልሳ ስምንት ሰዎች ኢትዮጵያውያን እና አንድ የአሜሪካ ዜጋ ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ ሰላሳ ስምንት (138) ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ አራት (4) ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ አራት (4) ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ አስራ አንድ (11) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ ስድስት (6) ሰዎች አማራ ክልል፣ አንድ (1) ሰው ከሐረሪ ክልል እና አምስት (5) ሰዎች ከሶማሊ ክልል ናቸው።

የላቦራቶሪ ውጤቶች እንደሚያሳዩት በሕብረተሰቡ ውስጥ ባለው የቫይረስ ስርጭት ምክንያት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነው። ለዚህም ማሳያ ምንም አይነት የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ወይም በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው ቫይረሱ በምርመራ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት በአዲስ አበባ አንዲሁም በክልሎች እየጨመረ ይገኛል። በመሆኑም እኛ ወይም የምንወደው ሰው ቀጥሎ በቫይረሱ የሚያዘው ሰው ልንሆን እንደሚችል በመገንዘብ  ከመቼውም ግዜ በላይ በመጠንቀቅ ስርጭቱን ማቆም እንችላለን። በዚህ ወረርሽኝ አንዳችን ለአንዳችን ዘብ በመቆም የኮሮና ቫይረስ የመከላከያ ዘዴዎችን ለመተግበር አንዳችን ስንዘናጋ ሌላችን ካስታወስን ህይወት ልናተርፍ እንችላለን። በመሆኑም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን አንዱን ዘዴ ከሌላው ሳናማርጥ በሙሉ መተግበር ይገባናል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የአንድ የ35 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊ ህይወት አልፏል። ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል በተደረገ ምርምራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ዘጠኝ (19) ደርሷል፡፡ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡  

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ ሁለት (12) ሰዎች (10 ከአማራ ክልል እና 2 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 262 ነው።

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ131,368
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ5798
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ169
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው1522
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር18
አዲስ ያገገሙ12
በአጠቃላይ ያገገሙ262
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ19
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር1805

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *