Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ግንቦት-27

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5141 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃምሳ (150) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,636 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 94 ወንድ እና 56 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ3 እስከ 72 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 147 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሶስቱ የአሜሪካ ዜጎች ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ ሃያ ስድስት (123) ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ አንድ (1) ሰው ከአፋር ክልል፣ ሁለት (2) ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ ሶስት (3) ሰዎች ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ ሁለት (2) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ አስራ ሶስት (13) ሰዎች አማራ ክልል እና ስድስት (6) ሰዎች ከሶማሊ ክልል ናቸው።

የላቦራቶሪ ውጤቶች እንደሚያሳዩት በሕብረተሰቡ ውስጥ ባለው የቫይረስ ስርጭት ምክንያት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነው። ለዚህም ማሳያ የመጀመሪያው ሰው በቫይረሱ መያዙ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ሁለት ወራት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ300 ፐርሰንት በላይ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት የታከሚዎችን ቁጥር በመጨመሩ እንደ ሚሊኒየም አዳራሽ አይነት የለይቶ ማከሚያዎች ታካሚዎችን እንዲቀበሉ ማድረግ ተጀምሯል፡፡

ስለዚህ ሕብረተሰቡ የእጅ ንጽኅናውን በመጠበቅ፣ በቤት በመቆየት ካለተቻለ ደግሞ ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ባለመገኘት፣ ከማንኛውም ሰው በ 2ሜትር አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ራሱንና የሚወዳቸውን ሁሉ ከቫይረሱ እንዲጠብቅ የጤና ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማሳሰብ ይወዳሉ፡፡

የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ተገኝቶበት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ህክምና ሲደርግለት የነበረ፣ ከዚህ ቀደም ተጓዳኝ ህመም ያለበት እና በፅኑ ህክምና ላይ የነበረ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ በትላንትናው ዕለት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ስምንት (18) ደርሷል፡፡ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡  

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አራት (4) ሰዎች ከአዲስ አበባ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 250 ነው።

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ                                                     

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ125,570
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ5,141
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ150
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው1,366
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር16
አዲስ ያገገሙ4
በአጠቃላይ ያገገሙ250
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ18
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር1,636

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 27 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *