ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,932 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ ሰባት (87) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,344 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 59 ወንድ እና 28 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ10 እስከ 70 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ስልሳ ሰባት (67) ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ ሁለት (2) ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ ስድስት (6) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ ሰባት (7) ሰዎች አማራ ክልል፣ ሐራሪ ክልል አንድ (1) ሰው እና አራት (4) ሰዎች ከሶማሊ ክልል ናቸው።
የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የተጋላጭነት ሁኔታ | ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው | 28 |
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው | 18 |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው | 41 |
ድምር | 87 |
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሁለት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። የመጀመርያው የ30 ዓመት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን ሁለተኛዋ የ56 ዓመት በአዲስ አበባ የተጓዳኝ ህመም ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው። ሁለቱ ግለሰቦች ህይወታቸው ያለፈና ለአስክሬን ምርመራ ወደ ሆስፒታል በመጡበት ጊዜ በተደረገ ምርምራ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ናቸው። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ አራት (14) ደርሷል፡፡ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል።
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ አራት ሰዎች (ስድስት ከኦሮሚያ ክልል እና ስምንት ከሶማሊ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 231 ነው።
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 116,309 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 3,932 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 87 |
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው | 1,097 |
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር | 8 |
አዲስ ያገገሙ | 14 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 231 |
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 14 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 1344 |
የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።
- መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
- መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
- መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
- መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ.ም