ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2926 የላብራቶሪ ምርመራ ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,257 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 51 ወንድ እና 34 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1ወር እስከ 65 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰባ ሁለት (72) ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ አራት (4) ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ አምስት (5) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ አንድ (1) ሰው አማራ ክልል እና ሶስት (3) ሰዎች ከሶማሊ ክልል ናቸው።
የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የተጋላጭነት ሁኔታ | ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው | 19 |
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው | 18 |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው | 48 |
ድምር | 85 |
የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ተገኝቶበት በኤካ ኮተቤ ህክምና ሲደርግለት የነበረ፣ ከዚህ ቀደም ተጓዳኝ ህመም ያለበት እና በፅኑ ህክምና ላይ የነበረ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ በትላንትናው ዕለት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ሁለት (12) ደርሷል፡፡ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ስምንት (8) ሰዎች (ሶስት ከኦሮሚያ ክልል እና አምስት ከአዲስ አበባ) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 217 ነው።
የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 112,377 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 2926 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 85 |
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው | 1,026 |
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር | 4 |
አዲስ ያገገሙ | 8 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 217 |
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 12 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 1257 |
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።
- መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
- መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
- መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
- መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም