Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ -ግንቦት 23

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2836 የላብራቶሪ ምርመራ 109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,172 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 61 ወንድ እና 48 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ 5 እስከ 70 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው 99 ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል እና 3 ሰዎች ከሐረሪ ክልል ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተጋላጭነት ሁኔታቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው2
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው13
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው94
 ድምር109

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የሶስት ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል። አንደኛዋ የ29 ዓመት በትግራይ ክልል የሰቲት ሁመራ ነዋሪ፣ ሁለተኛ የ75 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ እና ሶስተኛየ55 ዓመት በደቡብ ክልል የከፋ ዞን ነዋሪ (በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ የመጣ) ሲሆኑ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ አንድ (11) ደርሷል፡፡ የመጀመሪያ ሁለቱ ግለሰቦች በሆስፒታል ውስጥ ህክምና ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ሶስተኛው ህይወቱ ያለፈና ለአስክሬን ምርመራ ወደ ሆስፒታል የመጣና በተደረገልት ምርምራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡  

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አንድ (1) ሰው ከትግራይ ክልል ያገገም ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 209 ነው።

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ109451
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ2836
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ109
በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው950
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር4
አዲስ ያገገሙ1
በአጠቃላይ ያገገሙ209
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ11
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር1172

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።  

  • መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
  • መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 23 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *