Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ሚያዝያ-27

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1047 የላብራቶሪ ምርመራ አምስት (5) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መቶ አርባ አምስት (145) ደርሷል፡፡ የላብራቶሪ ምርመራው የተደረገው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ ባዮቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ላብራቶሪ፣ በአርሲ ዩኒቨርስቲ ላቦራቶሪ፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ እና በጅማ ዩኒቨርስቲ ሜዲካል ማዕከል የተከናወነ ነው፡፡ በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ ስድስት (16) ሰዎች (15 ከአዲስ አበባ እና 1 ከአማራ ክልል)  ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና አንድ (91) ነው። የዕለቱ ታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታም እንደሚከተለው ቀርቧል፣

ተ.ቁዜግነትመኖሪያ ቦታእድሜፆታየውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክበበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት
1ኢትዮጵያዊአዲስ አበባ75ሴትየላቸውምበመጣራት ላይ ያለ (በጤና ተቋም  ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን ከተወሰደ ናሙና የተገኘ)
2ኢትዮጵያዊአፋር25ወንድከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
3ኢትዮጵያዊአፋር22ወንድከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ
4ኢትዮጵያዊአዲስ አበባ8ሴትየላትምያላት
5ኢትዮጵያዊኦሮሚያ፣ ባቱ19ሴትየላትምያላት

ከላይ የተጠቀሱት የ75 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት በተጓዳኝ ህመም በሆስፒታል ውስጥ ተኝተው ሲታከሙ የነበሩ ሲሆን በገጠማቸው የመትንፈስ ችግር ምክንያት በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተጠርጥረው ምርመራ ናሙና ከተወሰደ በኋላ በምርመራ ውጤት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከመረጋገጡ በፊት ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል። የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ  የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ25,135
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ1047
በዛሬው  ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ5
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ48
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ0
አዲስ ያገገሙ16
በአጠቃላይ ያገገሙ91
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ4
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር145

የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ ከመተግበር መዘናጋት እንደሌለበት ጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጥብቅ ያሳስባሉ፡፡ ሕብረተሰቡ በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግና አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል እናሳስባለን፡፡

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ሚያዝያ 27፣ 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *