Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ግንቦት-22

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5034 የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠና አምስት (95) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አንድ ሺህ ስልሳ ሶስት (1,063) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 71 ወንድ እና 24 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ 15 እስከ 80 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ዘጠና አራት ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንድ የህንድ ዜጋ ይገኛል። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሃምሳ ስድስት (56) ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ ሶስት (3) ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ አንድ (1) ሰው ከአፋር ክልል ፣ አምስት (5) ሰዎች ከአማራ ክልል፣ ሃያ ሁለት (22) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ ሶስት (3) ሰዎች ከሐረር ክልል፣ ሁለት (2) ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና ሶስት (3) ሰዎች ከሶማሊ ክልል ናቸው።

የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተጋላጭነት ሁኔታቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው30
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው4
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው61
 ድምር95

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አስራ አንድ (11) ሰዎች (ሁለት ከትግራይ ክልል እና ዘጠኝ ከአፋር ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ሁለት መቶ ስምንት (208) ነው።

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ106,615
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ5,034
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ95
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ845
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር5
አዲስ ያገገሙ11
በአጠቃላይ ያገገሙ208
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ8
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር1063

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።   

  • መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
  • መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 22 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *