ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5015 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት (137) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስምንት (968) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 86 ወንድ እና 51 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ 4 እስከ 75 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ሰዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ ዘጠኝ (109) ሰዎች ከአዲስ አበባ ፣ አንድ (1) ሰው ከአፋር ክልል ፣ ሁለት (2) ሰዎች ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ አስራ ሰባት (17) ሰዎች ከአማራ ክልል እና ስምንት (8) ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ናቸው።
የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የተጋላጭነት ሁኔታ | ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው | 20 |
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው | 8 |
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው የታወቅጋር ግንኙነት የሌላቸው | 109 |
ድምር | 137 |
በተጓዳኝ ህመም ምክንያት ህክምና ላይ የነበሩ የ62 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወንድ ለኮሮና ቫይረስ በሽታ በተደረገ ምርመራ ናሙና ከተወሰደ በኋላ የምርመራ ውጤት ሳይደርስ ህይወታቸው አልፏል። በምርምራው ውጤትም ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ስለተረጋገጠ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ስምንት (8) ደርሷል፡፡ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡
በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ስድስት (6) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ዘጠና ሰባት (197) ነው።
የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 101,581 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 5015 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 137 |
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ | 761 |
በፀና የታመሙ ሰዎች ቁጥር | 4 |
አዲስ ያገገሙ | 6 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 197 |
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 8 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 968 |
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።
- መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
- መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
- መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
- መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም