Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ግንቦት-14

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3645 የላብራቶሪ ምርመራ ሰላሳ (30) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አራት መቶ ሃያ ዘጠኝ (429) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 26 ወንድ እና 4 ሴት ናቸው፡፡ በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ 15 እስከ 60 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አስራ ስምንት (18) ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ ሶስት (3) ሰዎች ከአፋር ክልል ፣ አራት (4) ሰው ከኦሮሚያ ክልል፣ ሶስት (3) ሰዎች ከትግራይ ክልል እንዲሁም ሁለት (2) የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ናቸው፡፡

የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተጋላጭነት ሁኔታቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው9
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው17
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው4
 ድምር30

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አምስት (5) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ ስምንት (128) ነው።

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ73,164
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ3645
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ30
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ294
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ0
አዲስ ያገገሙ5
በአጠቃላይ ያገገሙ128
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ5
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር429

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልፈጥር በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዓሉን ስናከብር የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለመከላከል የሚከተሉትን ተግባራት እንፈፅም

  • ዘካተል ፊጥር በምንሰጣጥበት ጊዜ አካላዊ ርቀታችንን እንጠብቅ
  • በበዓል ሰሞን መዘያየር ባህላችን ቢሆንም የዘንድሮዉን ኢድ በስልክ በመጠያየቅ እናሳልፍ
  • ለበዓል ግብይት ስንወጣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ወይም ጨርቅ እናድርግ
  • አከባቢያችን ባለ ገበያ አካላዊ ርቀትቀታችንን ጠብቀን እንገበያይ እንዲሁም ገንዘብም ሆነ ሌሎች ቁሳቁሶቸን ከነካን በኋላ እጃችንን በውሃና ሳሙና ወይም አልኮል ባለዉ የጀርም ማፅጃ(ሳኒታይዘር) እናፅዳ፣

ይህንንና ሌሎች የጥንቃቄ ተግባራትን በመፈፀም ቤተሰባችንንና ወዳጆቻችንን ከቫይረሱ እንጠብቅ::

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *