ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1758 የላብራቶሪ ምርመራ አምስት (5) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር መቶ አርባ (140) ደርሷል፡፡ የላብራቶሪ ምርመራው የተደረገው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት፣ በብሄራዊ የእንስሳት ጤና በሽታዎች ምርመራ ማዕከል፣ በአርማውር ሃንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በኢንተርናሽናል ክሊኒካል ላብራቶሪስ፣ በአዳማ የህብረተሰብ ጤና ምርምርና ሪፈራል ላብራቶሪ፣ በአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በሐረማያ ዩኒቨርስቲ ላቦራቶሪ እና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ላብራቶሪ የተከናወነ ነው፡፡ የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታም እንደሚከተለው ቀርቧል፣
ተ.ቁ | ዜግነት | መኖሪያ ቦታ | እድሜ | ፆታ | የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ | በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት |
1 | ኢትዮጲያዊ | – | 24 | ወንድ | ከፑንትላንድ የተመለሰና በጂግጂጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | |
2 | ኢትዮጲያዊ | – | 23 | ወንድ | ከፑንትላንድ የተመለሰና በጂግጂጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | |
3 | ኢትዮጲያዊ | – | 20 | ወንድ | ከፑንትላንድ የተመለሰና በጂግጂጋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ | |
4 | ኢትዮጲያዊ | ባህር ዳር | 17 | ወንድ | ያለው | |
5 | ስዊድናዊ (ትውልደ ኢትዮጵያዊ ) | – | 19 | ወንድ | ከስዊድን የተመለሰና በአዲስ አበባ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ |
በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ
አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 24,088 |
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ | 1758 |
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ | 5 |
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ | 60 |
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ | 0 |
አዲስ ያገገሙ | 0 |
በአጠቃላይ ያገገሙ | 75 |
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ | 3 |
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ | 2 |
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር | 140 |
የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመከላከል ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ ከመተግበር መዘናጋት እንደሌለበት ጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጥብቅ ያሳስባሉ፡፡ ሕብረተሰቡ በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተው፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግና አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል እናሳስባለን፡፡
በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ
የጤና ሚኒስትር
ሚያዝያ 26፣ 2012 ዓ.ም