Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ግንቦት-13

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3747 የላብራቶሪ ምርመራ ዘጠኝ (9) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት መቶ ዘጠና ስምንት (398) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 8 ወንድ እና 1 ሴት ናቸው፡፡ በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ 20 እስከ 49 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሶስት (3) ሰዎች ከአዲስ አበባ (ሁለት በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እና አንድ ሰው የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው)፣  ሁለት (2) ሰዎች ከአፋር ክልል (የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው)፣ አንድ (1) ሰው ከሶማሊ ክልል (የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው እና በጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ ያሉ፣ አንድ (1) ሰው ከትግራይ ክልል (የውጭ ሃገር ጉዞ ታሪክ ያለው እና በማይካድራ ለይቶ ማቆያ ያለ) እንዲሁም ሁለት (2) ሰዎች ከአማራ ክልል (የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው እና መተማ ለይቶ ማቆያ ያሉ)  ናቸው፡፡

የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተጋላጭነት ሁኔታቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው5
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው2
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው2
 ድምር9

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አንድ (1) ሰው ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ ሶስት (123) ነው።

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ69,507
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ3747
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ9
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ268
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ0
አዲስ ያገገሙ1
በአጠቃላይ ያገገሙ123
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ5
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር398

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ  ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።   

  • መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
  • መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *