Categories
Amharic

የኮሮና ቫይረስ (የኮቪድ-19) በሽታ ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ ግንቦት-11

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3271 የላብራቶሪ ምርመራ አስራ አራት (14) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት መቶ ስልሳ አምስት (365) ደርሷል፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 11 ወንድ እና 3 ሴት ናቸው፡፡ በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ 9 እስከ 68 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ዘጠኝ (9) ሰዎች ከአዲስ አበባ (አንድ (1) የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ ፣ ሰባት (7) በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ አንድ (1) ሰው የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌለው)፣ አንድ (1) ሰው ከትግራይ ክልል (የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ፣ መቐለ ለይቶ ማቆያ ያለ) ፣ አንድ (1) ሰው ከኦሮሚያ ክልል (የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ) እንዲሁም ሶስት (3) ሰዎች ከሶማሊ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ)  ነው፡፡

ማስተካከያ፦ በትላንትናው ዕለት በወጣው ዕለታዊ መግለጫ ከአማራ ክልል (ሰሜን ሸዋ ዞን፤ አጣየ ከተማ ለይቶ ማቆያ) ቫይረሱ በምርመራ የተገኘበት  ተብሎ የተገለፀው በግንቦት 9 ቀን በወጣው መግለጫ ላይ ተጠቅሶ የነበር መሆኑን እና በትላንትናው በድጋሚ ሪፖርት የተደረገ ነው። በመሆኑም በትላንትናው ዕለት ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 34 መሆኑን ከይቅርታ ጋር እንገልጻለን።

የዕለቱ ታማሚዎች የተጋላጭነት ሁኔታ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተጋላጭነት ሁኔታቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው6
በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው7
የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው1
 ድምር14

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት አራት (4) ሰዎች (3 ከሶማሊ ክልል እና 1 ከአፋር ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ (120) ነው።

 በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ

አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ62,300
በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ3271
በዛሬው ዕለት በበሸታ መያዛቸው በላብራቶሪ የተረጋገጠ14
በአጠቃላይ በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ከህክምና ውስጥ ያሉ238
በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ0
አዲስ ያገገሙ4
በአጠቃላይ ያገገሙ120
በበሽታው ሕይወታቸው ያለፈ5
ወደ ሀገራቸው የተመለሱ2
እስከ አሁን ድረስ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር365

የላብራቶሪ ምርመራ ናሙናዎች ከተለያዩ ይበልጥ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከጤና ተቋማት፣ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ካላቸው ሰዎች እንዲሁም በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ካሉ ሰዎች ተወስዶ የተከናወነ ነው፡፡

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ  ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ሕብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳስባሉ። በበሽታው መያዛችን ዕለት-ተዕለት በምናደርገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን የ’’መ’’ ህጎች ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንድንከላከል በጥብቅ እናሳስባለን።   

  • መራራቅ፡ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ፡ እጅን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት፡ አስገድጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት እንዲሁም
  • መሸፈን፡ ከቤታችን ወጥተን ስንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም

በማንኛውም ሰዓት ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ሪፖርት ለማድረግ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በ952 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 በመደወል ወይም በኢሜል አድራሻችን ephieoc@gmail.com በመጠቀም ወይም ባሉበት ክልል በተዘጋጁ ነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ ጤና ተቋማት በስልክ እንዲያሳውቁ እንጠይቀለን፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

የጤና ሚኒስትር

ግንቦት 11 ቀን 2012 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *